ፍርድ ቤት
ፍርድ ቤት ፍርድ የመስጠት ስልጣን ያለው የ መንግስት አካል ነው። ከሶስቱ ከፍተኛ የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አውጭ፣ ህግ ተርጓሚ እና ህግ አስፈጻሚ አንዱ ነው። ይህ አካል ህግ ተርጓሚ የሚባለው ነው። የወንጀለኛ መቅጫ ህግ፣ ሲቪል ህግ፣ አስተዳደራዊ ህግ እና ሌሎች ህጎችን በየህግ የበላይነት ላይ መሰረት በማድረግ ይተረጉማል።
ታሪክ ለማስተካከል
ፍርድ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ክንውን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለምዶ ወይም ባህል በበላ ልበልሃ እየታገዘ በመንደር ሽማግሌዎች ወይም በሀገረ ገዥዎች ፊት ይቀርብ ነበር። ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ወዲህ በዘመናዊው የመንግስት መዋቅር የህግ ተርጓሚነትን የመንግስት ሰልጣን ተሰጥቶት መንግስት በሾማቸው ዳኞች ይመራል።
ገለልተኝነት ለማስተካከል
ይህ አካል በዘመናዊዉ የዴሞክራሲ መርህ ከየትኞቹም የመንግስት አካላት በገለልተኝነት ይንቀሳቀሳል። ሶስቱም የመንግስት አካላት ጣልቃ መግባት አይችሉም። በሃገሪቱ የሚገኝ ማንኛውም ዜጋ፣ አካል፣ ወይንም ተቋም ይዳኝበታል።
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchካናዳየአድዋ ጦርነትውክፔዲያ ውይይት:ምንጭጌዓፄ ቴዎድሮስአበበ ቢቂላኤችአይቪሥርዓተ ነጥቦችኢትዮጵያገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችዳግማዊ ምኒልክስዕል:Guitar-cr.pdfቅዱስ ያሬድዘጠኙ ቅዱሳንአፈወርቅ ተክሌ2ኛው ዓለማዊ ጦርነትላሊበላየአክሱም ሐውልትልዩ:RecentChangesአዲስ አበባጉራጌጀጎል ግንብእርዳታ:ይዞታጥላሁን ገሠሠመንግስቱ ኃይለ ማርያምመዝገበ ቃላትአቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞየጋብቻ ሥነ-ስርዓትУчастник:Zoner30ሀዲስ ዓለማየሁቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴውክፔዲያአማርኛዩ ቱብገበጣፋሲል ግቢየጢያ ትክል ድንጋይትግራይ ክልል