ዕፅዋት ከሕያዋን ነገሮች አምስቱ ዋና ዘርፎች አንዱ ናቸው። ምግበለፊ ውኑክለስ ናቸው፣ ይህም ማለት የራሳቸውን ምግብ ይሰራሉ እና ውስብስብ ወይም ባለኑክለስ ህዋስ (ሴሎች) ያላቸው ናቸው። አብዛኞቹ ዕፅዋት ከስፍራ ወደ ስፍራ መዛወር እንደ እንስሶች አይችሉም። ሲበቅሉ ግን እጅግ ቀስ ብለው ይዞራሉ።

ቢጫ አበባ

በዕፅዋት ዘርፍ ውስጥ ታዋቂ አይነቶች ዛፍዕፅቊጥቋጥሣርሐረግፈርንሽበትአረንጓዴ ዋቅላሚ ይገኛሉ። በዕፅዋት ጥናት ዘንድ፣ አሁን 350,000 ያሕል የዕፅዋት ዝርያዎች ይኖራሉ። ፈንገስ እና አረንጓዴ ያልሆነ ዋቅላሚ ግን እንደ ዕፅዋት አይቆጠሩም።

አብዛኛዎቹ ዕፅዋት በመሬት ውስጥ ይበቅላሉ፣ አገዳቸው ከላይና ሥራቸው በታች አላቸው። አንዳንድ በውኃ ላይ ሰፋፊዎች ናቸው። ውኃና ምግብ የሚያገኙ በሥሮቻቸው በኩል ነው፤ ከዚያ በአገዳ ወጥተው እስከ ቅጠሎች ድረስ ሲጓዙ ነው። በቅጠሎች ውስጥ በሚገኙት ትንንሽ ቀዳዳዎች ውኃ በፀሐይ ዋዕይ በመትነን፣ ውኃው በአገዳው መንገድ ምግብን ከታቹ ወደ ላይ ይስባል። ይህም ስበተ ቅጠላበት ይባላል።

ዕፅዋት ምግብን እንዲሠሩ፣ የሚያስፈልጉዋቸው የፀሐይ ብርሃን፣ ካርቦን ክልቶኦክሳይድ፣ የመሬት ማዕድንና ውኃ ነው። አረንጓዴው ሃመልሚል (ክሎሮፊል) የፀሐይቱን አቅም ይወስዳል።

እንደ እንሥሣት፣ ዕፅዋትም የእንስትና የተባእት የዘር ህዋስ (gamete) ያመነጫሉ። በተጨማሪ፣ ብዙ የዕፅዋት አይነቶች ወሲባዊ በማይሆን ዘዴ መስፋፋትና መባዛት ይችላሉ። ይህ እፃዊ ተዋልዶ ይባላል።

ሥነ ሕይወታዊ ክፍፍሎች ለማስተካከል

ሥነ ሕይወት ጥናት ዘንድ፣ ዕፅዋት አንድ የሕይወት ስፍን ሲሆን የሚከተሉ ክፍለስፍኖች ብውስጡ ይመደባሉ፦

የመሬት ሃመልማል Embryophyteሃመልማል Viridiplantae
አረንጓዴ ዋቅላሚ
ሌላ ዋቅላሚ Biliphyta (ባብዛኛው እንደ አትክልት አይመደቡም)
ክፍለስፍንሮማይስጥመኖሪያየባሕርይ ልዩነትዝርያ ቁጥር
ዱኬ ቀንድAnthocerotophyta[1]ዓለም አቀፍቀንድ ያለ ዱኬ ወለድ፣ ሸንዳ የለሽ100-300+
ሳረንስትBryophytaአለም አቀፍዘለቄታዊ ቅርንጫፍ የለሽ ዱኬ ወለድ፣ ሸንዳ የለሽ12000 ያህል
የባሕር ድንጋይ አረንጌዴ ዋቅላሚCharophytaጨው አልባ ውሆች1000 ያህል
የባሕር አረንጓዴ ዋቅላሚChlorophytaአለም አቀፍ7000 ያህል
የንጉሥ አሚዶ ዘምባባ ክፍለስፍንCycadophytaገሞጂዎችባዶ ዘር፣ የድርብርብ ቅጠል አናት100-200
የብር ባሕርኮክ (ጊንኮ)Ginkgophytaቻይናባዶ ዘር ዛፍ1 ብቻ
ሰማያዊ ዋቅላሚGlaucophytaጨው አልባ ውሆች13
የመሊንጆ ክፍለስፍንGnetophytaአንዳንድ አገሮችባለዘር፣ ሸንዳማ እንጨት70
የበትረሳረንሰት ክፍለስፍንLycopodiophyta

Lycophyta

አለም አቀፍነጠላ ሸንዳ ዕጽ1290
ክንንብ ዘር፣ አባቢ አትክልትMagnoliophytaአለም አቀፍአበባ፣ ፍሬ፣ ሸንዳማ እፅ300,000
ጉብ ዕጽMarchantiophyta,[2]

Hepatophyta

አለም አቀፍኢዘለቄታዊ፣ ቅርንጫፍ የለሽ ዱኬ ወለድ፤ ሸንዳ የለሽ9000 ያህል
ዘረ ቅምብብPinophyta

Coniferophyta

አለም አቀፍባለዘር ቅምብብ፣ ሸንዳማ እንጨት629
ፈርንMonilophytaአለም አቀፍቀዳማይ ብቃይ ህዋስ ወለድ እፅ፣ ሸንዳማ9000 ያህል
ቀይ ዋቅላሚRhodophytaዓለም አቀፍ7000 ያህል
ድምሩ፦ 14
  1. ^ Mauseth, James D. (2012). Botany : An Introduction to Plant Biology (5th ed.). Sudbury, MA: Jones and Bartlett Learning. ISBN 978-1-4496-6580-7.  p. 489
  2. ^ Crandall-Stotler, Barbara; Stotler, Raymond E. (2000). "Morphology and classification of the Marchantiophyta". in A. Jonathan Shaw & Bernard Goffinet (Eds.). Bryophyte Biology. Cambridge: Cambridge University Press. p. 21. ISBN 0-521-66097-1.