የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን (ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ.) በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ውስጥ የሥነምግባር መከታተያ ኮሚሽን ነው። የኮሚሽኑ ተጠሪነት በቀጥታ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው።[1] የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ክቡር አቶ ዓሊ ሱለይማን ሲሆኑ ም/ኮሚሽነሩ ደግሞ ክቡር አቶ ወዶ አጦ ናቸው። ኮሚሽኑ «ሥነምግባር» (እንግሊዝኛ፦ Ethics) የተባለ በዓመት አራት ጊዜ የሚታተም መፅሄት እና «መስታወት» (እንግሊዝኛ፦ Insight) የተባለ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚወጣ ኒውስሌተር አለው።

የኮሚሽኑ ምልክት

አመሠራረት ለማስተካከል

እ.ኤ.አ. በ1996 በብሔራዊ ደረጃ የተጀመረው የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም የሥነምግባር ንዑስ ፕሮግራምን በውስጡ የያዘ ነበር።[2] የስነምግባር ንዑስ ፕሮግራም አንድ ፕሮጀክት ኮሚሽኑን ማቋቋም ነበር።[2] የፕሮጀክቱም ስም የስነምግባር መከታተያና ማዕከላዊ አካል ማቋቋሚያ ፕሮጀክት የሚል ነበር። በዚህም መሰረት የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ግንቦት 16 ቀን 1993 ዓ.ም. በአዋጅ ተቋቋመ።[2]

መዋቅር ለማስተካከል

ኮሚሽኑ ዘጠኝ ዳይሬክቶሬቶችና ሁለት አገልግሎቶች አሉት። በተጨማሪም የኮሚሽኑን ውስጣዊ አሠራርን የሚከታተል የሥነምግባር መከታተያ ጽ/ቤት አለ።[3] ይህም ጽህፈት ቤት በአቶ ሃረጎት አብርሃ ይመራል።[3] የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እስከ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. ድረስ 315 ሠራተኞች ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 101 ሴቶች ናቸው።[4]

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ ይገኛል።[5] በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘው የኮሚሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተመረቀው በመጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. ሲሆን በአሁኑ ወቅት 21 ሠራተኞች አሉት።[5]

ዳይሬክቶሬቶች ለማስተካከል

ዳይሬክቶሬትዳይሬክተር
የሀብት ማሳወቂያ እና ምዝገባ ዳይሬክቶሬት[6]አቶ ግርማ ወርቁ[6]
የሙስና ወንጀል ምርመራ እና ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት[7]አቶ ገብሩ ገበየሁ[7]
የሙስና መከላከል ዳይሬክቶሬት[8]አቶ አክልሉ ሙሉጌታ[8]
የሥነ ምግባር ትምህርት እና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት[9]አቶ ብርሃኑ አሰፋ[9]
የሥነ ምግባር አውታሮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት[10]አቶ ብርሃኑ ክፈተው[10]
የሰው ሀብት ሥራ አመራር[11]አቶ መኮንን ዘገዬ[11]
ዕቅድ፣ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት[12]አቶ ሙላት ሸዋታጠቅ[12]
የጥናት እና የለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት[13]አቶ ተስፋዬ ሻሜቦ (ተጠባባቂ)[13]
የኦዲት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት[14]አቶ ፋኖሴ ሀሰን[14]

አገልግሎቶች ለማስተካከል

አገልግሎትኃላፊ
የህግ አገልግሎት[15]አቶ ብሌን ግርማይ (ተጠባባቂ)[15]
ጠቅላላ አገልግሎት[16]ጥላዬ የትዋለ[16]

በጀት ለማስተካከል

ኮሚሽኑ ከመንግስት በ፳፻፪ ዓ.ም. 16.23 ሚሊዮን ብር፣ በ፳፻፫ ዓ.ም. 26 ሚሊዮን 93 ሺህ 930 ብር፣ በ፳፻፬ ዓ.ም. ደግሞ 34 ሚሊዮን 840 ሺህ ብር የተመደበለት ሲሆን ከሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት በየዓመቱ የሚያገኘው ገንዘብም አለ።[4]

ማመዛገቢያ ለማስተካከል

  1. ^ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተጠሪነት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  2. ^ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመሠራረት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  3. ^ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  4. ^ የኮሚሽኑ በጀትና የሰው ኃይል Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  5. ^ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  6. ^ የሀብት ማሳወቂያ እና ምዝገባ ዳይሬክቶሬት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  7. ^ የሙስና ወንጀል ምርመራ እና ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  8. ^ የሙስና መከላከል ዳይሬክቶሬት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  9. ^ የሥነ ምግባር ትምህርት እና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  10. ^ የሥነ ምግባር አውታሮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  11. ^ የሰው ሀብት ሥራ አመራር Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  12. ^ ዕቅድ፣ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  13. ^ የጥናት እና የለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  14. ^ የኦዲት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  15. ^ የህግ አገልግሎት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)
  16. ^ ጠቅላላ አገልግሎት Archived ኦክቶበር 16, 2013 at the Wayback Machine (በነሐሴ ፳፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ)

የውጭ መያያዣ ለማስተካከል