ወልቃይት

ትግራይ ውስጥ የሚገኝ የትግራይ መሬት

ወልቃይት ጠገዴ ማነው?“የወልቃይት ባህልና የማንነት ጥያቄ” የሚለው ፅሁፋ በገጽ 4,2ኛው አንቀጽ ላይ “ስለዚህ የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባርወልቃይትን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያለውንታሪክ በዜሮ ብናባዛው፤ የህዝበ-ውሳኔው ውጤት ከትግራይ ጋርመኖር የሚሹ ወልቃይቴዎች በሰፊ ልዩነት ሊያቸንፉ መቻላቸውንያበስር ነበር” ይላል። ነገር ግን ይህ የአቶ ሃይሉ የሺወንድምምኞትና ድምዳሜ ወይም ህወሃታዊ ተልዕኮ ከታሪክና ከተጨባጩየወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ አቋምና ምርጫ ፍጹምእንደሚቃረንና እንደሚጋጭ በሁለት ቀደምት የህወሃት አባላትየቀረቡ ምስክርነቶች አጥጋቢ መልስ ስለሚሰጡ እነርሱንእንመልከት።ኢትዮጵያውያን እንደ ዛሬው ህወሃት በለጠፈብን የብሔር ታርጋምክንያት የጎሪጥ መተያየት ሳንጀምርና ሃገራችን ጎጥ ጎጥከመሽተቷ 37 ዓመታት በፊት በትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን በኩልለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የቀረበው “ወልቃይት ጠገዴማነው?” ጥያቄ በወቅቱ የነበሩት ኩሩና በማንነታቸው ላይ ፍጹምብዥታ ያልነበራቸው ወገኖቻችን የህወሃት ወኪል ለነበረውናጥያቄውን ይዞ ለመጣው ለአቶ መኮንን ዘለለው በማያዳግምሁኔታ መልሰውለት እንደነበር ታሪክ ህያው ምስክር ነው። በወቅቱየነበረውን ሁኔታ የህወሃት ነባር አባልና የፋይናንስ ኋላፊ የነበሩትአቶ ገብረመድህን አርአያ በዲሴምበር 22, 2015 ኢትዮ-ሚዲያና ጎልጉል ድረ-ገፅ ላይ “በወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምትበአማራው ላይ ህወሃት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል” በሚልባወጡት ጥልቅ ሰነድ በገጽ 2 ላይ፤“በሪጅን 1 የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው፣ በአባቱ ወልቃይትፀገዴ፣ በእናቱ ሽሬ የሆነው መኮንን ዘለለው፣ የተወጠነውንትልእኮ ይዞ ወልቃይት ፀገዴ ፀለምት እየተዘዋወረ ህዝቡንበመሰብሰብ ይህ መሬት የትግራይ መሬት ስለሆነ እናንተከእንግዲህ ወዲህ የሰሜን ጎንደር ዜጎች አይደላችሁም፣የትግራይ መሬት ስለሆነ እንኖራለን ካላችሁ ትግሬዎችመሆናችሁን አምናችሁ ተቀበሉ፤ የትግራይ ዜጎች አይደለንም፣ሰሜን በጌምድር የትግራይ አይደለም ካላችሁ ደግሞ የድርጅቱንየህወሓትን ውሳኔ ተጠባባቁ፤ የምታምኑበትን አሁን ተናገሩበማለት ሲያስጠነቅቅ፣ ከህዝቡ በኩል ያገኘው መልስ ግን አንድነበር። የቀረበውን ሃሳብ ከህፃን እስከ አዋቂ፣ የወልቃይት ፀገዴናየፀለምት ህዝብ፣ እኛ የሰሜን በጌምድር (ጎንደር) አማሮች እንጂትግሬዎች አይደለንም፣ የታሪካችን ስር መሰረቱ የበጌምድርአማሮች ነን። ይህ ቆመህ የምትናገርበት መሬት ሰሜን በጌምድርይባላል። ከጥንቱ ታሪካችን 3 ብትነሳም ይህ መሬት ታሪካዊ ነው።ያለፉት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአትበመንግሥት እውቅና ያገኘ የጎንደር፣«”የበጌምድር” ጠቅላይግዛት እየተባለ የሚጠራ ነው። ዋና ከተማችን ደግሞ ጎንደርነው። የእናንተም ትግራይ ጠቅላይ ግዛት ይባላል፣ ዋና ከተማውደግሞ መቀሌ ነው። ስለዚህ ኣናንተ የተሓህት ታግዮች ጉዳዩንብታሱብበት ጥሩ ነው። ወደ እርስ በርስ ግጭያመራል።በተጨማሪም ታሪካዊ የወሰን ክልል አለን፣ እሱም ተከዜወንዝ ነው። የትግራይና በጌምድር የድንበር ክልሉ ተከዜ ወንዝነው። ከጥንት ጀምሮ የሁለቱ ኢትዮጵያውያን የድንበር ወሰንመሆኑን ልናረጋግጥ እንፈልጋለን በማለት በአንድነት ድምፅ ህዝቡራሱ አረጋገጠ።” በማለት ገልፀውታል።ይልቁንም በአቶ መኮንን ዘለለው በኩል ለቀረበላቸው የማንነትጥያቄ “የበጌምድር አማሮች ነን” የሚለውን የማያወላዳ ምላሽየሰጡ የማህበረሰቡ ታላላቅና የተከበሩ መሪዎች በአቶ ስዩምመስፍንና በአቶ ግደይ ዘራፅዮን መሪነት ታፍነው ወደ ትግራይመወሰዳቸውንና በሳሞራ የኑስ ትእዛዝ እንደተረሸኑ እራሳቸው አቶመኮንን ዘለለው ለኢሳት ቴሌቭዥን በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ላይበዝርዝር አጋልጠዋል። በዚህ “ወልቃይት ጠገዴ ማነው?”በሚለው የህወሃት ያልተቋረጠ ጥያቄ ዙሪያና ህዝባችንበሚሰጣቸው አንድ፤ ግልፅና ቀጥተኛ መልስ ምክንያት ወገናችንየጅምላ ግርፋቶች፤ መፈናቀሎች፤ እስራቶች፤ ግድያዎች፣ ስደቶች፣ቅስም ሰባሪና፣ ፀያፍ በደሎች ተፈፅመውበታል።ታዲያ ይህ ሁሉ ሰቆቃ አሁንም ሳያባራ የትግራዩ ነጻ አውጭቡድን እነሆ ዛሬም እንደገና በእነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም በኩል“ወልቃይት ጠገዴ ማነው?” ይለናል። አስቀድሞ በአቶ መኮንንዘለለው በኩል ቀርቦ ህዝባችንን ለእልቂት የዳረገው ህወሃታዊጥያቄ ዳግም ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ መጠየቅ ማለትአንድም ወገኖቻችን በማንነታቸው ጸንተው በመቆማቸውምክንያት የከፈሉትን መስዋእትነት እንደ “ውሻ ደም” በመቁጠርለመሳለቅ ወይም በህዝባችን ላይ ለተደገሰው ቀጣይ ህወሃታዊፍጅት ሰበብ ለማዛጋጀትና የጥፋት መንገድ ለመጥረግ የታለመይመስላል።የህወሃት ሆድ-አደሮች ምን እያሉን ነው?ወልቃይት ጠገዴ ማነው? ለሚለው የህወሃት መላዘን ወልቃይትጠገዴ ማህበረሰብ ምላሹ ከላይ በአይን እማኞችና በህያውምስክሮች እንደተረጋገጠ አይተናል። ታዲያ ለምን የዛሬዎቹተላላኪዎች “ስለዚህ የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ወልቃይትንከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያለውን ታሪክበዜሮ ብናባዛው፤ የህዝበ-ውሳኔው ውጤት ከትግራይ ጋር መኖርየሚሹ ወልቃይቴዎች በሰፊ ልዩነት ሊያቸንፉ መቻላቸውን ያበስርነበር” እያሉ ሌላውን ህዝብ ለማደናገር ይሞክራሉ? ለምንስበወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ በደል ላይ ይዘባበታሉ? የሚልጥያቄ መነሳቱ አይቀርም።ከዚህ የሆድ አደሮች ዘመቻ የምንረዳው ነገር ቢኖር ተላላኪዎቹቀደም ሲል በተደጋጋሚ እንገልጸው እንደነበረው ሁሉ ከህወሃትየተሰጣቸውን “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብን በማዳከምናበመከፋፈል ትግሪያዊነትን አሜን ብሎ እንዲቀበል” የማስቻልተልእኮ ለማሳካት በሚል በመላው ኢትዮጵያ በተለይም እንደጋምቤላ ባሉ አካባቢዎች በሚደረጉ የመሬት ዘረፋዎችናቅርምቶች (ወልቃይት ጠገዴ ለትግራውያን ብቻ ነው)ቢንበሻበሹም ውጤቱ ግን “ጉም መዝገን” ሆኖባቸዋል።ይልቁንም በሃገር ውስጥ የሚገኘው የወልቃይት ጠገዴማህበረሰብ ከምንግዜውም በላይ ተደራጅቶና ከመላው የአማራህዝብ ጋር አንድ ሆኖ ማንነቱ ለማስከበር ቆርጦና አምርሮ ሲነሳከህወሃት ይልቅ የተጨነቁት በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ስምድርጎ ሲቀበሉ የከረሙት ናቸው።ከህወሃት በኩል ልምጭ የተቆረጠበት የሚመስለው ሆድ-አደሩቡድን መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያንገሸገሸውንና ህወሃትን እስከአንገቱ ያነቀውን፤ ይልቁንም በህወሃት/ኢህአዴግ መንደር እውቅናአግኝቶ ከጠ/ሚ እስከ ተራ ካድሬ እየተቀባበለ የሚዘምርለትን“የመልካም አስተዳደር እጦት” በምትባል “የጦስ ዶሮ” በመታከክየወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ያነሳውን ዘርንና ትውልድንከጥፋት የመታደግና የአማራ ማንነቱን በትግሪያዊነት ከመተካትየማዳን ፈርጀ ብዙ ጥያቄ “የትግራይ ክልል ባለስልጣናትየአስተዳደር በደል ስለፈጸሙበት” ነው እያሉ ማፌዝ በወልቃይትጠገዴ ማህበረሰብ ቁስል በእሳት የጋለ ብረት እንደመስደድይቆጠራል።ያስተዛዝባልም።ይልቅስ አቶ ሃይሉና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው በወልቃይት ጠገዴማህበረሰብ ላይ የደረሰው በደል የዘር ማፅዳትና በትግሪያዊነትየመተካት ዓለም-አቀፍ ወንጀል መሆኑን የምትስቱትአይመስለንም። ይህን በማንነታችን ላይ የተፈጸመና በዓለም-አቀፍየፍርድ አደባባይ የሚያስጠይቅን ወንጀል በማኮሰስና “የትግራይክልል ባለስልጣናት የአስተዳደር በደል” አድርጎ በማቅረብከህወሃት ጋር የገጠማችሁን ኪሳራ ማወራረድ ወይምየሚቆረጥላችሁን ድርጎ ማሳደግ አትችሉም። ኪሳራችሁንማወራረድም ሆነ ሌላም ማድረግ የምትችሉት ለጌቶቻችሁእውነቱን በመናገር ብቻ ነው። ምክንያቱም የወልቃይት ጠገዴማህበረሰብ ጎንደሬ-አማራ መሆኑን በአንድ ድምጽ ያረጋገጠውናበማንነቱም ምክንያት ለሚመጣ ማንኛውም ነገር ዋጋ ለመክፈልዝግጁነቱንና ቁርጠኝነቱን በተግባር ያሳየው ገና “የትግራይ”የሚባሉ ገዥዎችና አስተዳደራቸው ከመፈጠሩ እጅግ አስቀድሞእንደነበር ከወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ባልተናነሰ እነ ስብሃትነጋ ጠንቅቀው ያውቃሉና እራሳችሁን አታታልሉ። ትዝብት ላይምአትውደቁ።በሌላ በኩል ምንም እንኳ ዛሬ ህወሃት እስከ አፍንጫውቢታጠቅና የሃገሪቱን መንግስታዊ ስልጣንና ሃብት እንዳሻውቢያዝና ቢናዘዝበትም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ዛሬምበማንነቱ ላይ ያለውን የቀደመ ጽኑ እምነትና የትውልዱንምስክርነት ማስለወጥ አልተቻለውም። እንግዲህ ለህወሃትና ለእነአቶ ሃይሉ የሺወንድም እውነታው እንደ እሬት መራራቢሆንባቸውም ታሪክ በደማቁ የመዘገበውና በእያንዳንዱየወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ህሊና ተጽፎ የሚገኘውና ለትውልድየምናስተላልፈው እውነታ ግን የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብህወሃት ዕርስታችንን ከመርገጡ በፊትም ሆነ በወረራበተቆጣጠረ ጊዜ በጎንደሬ-አማራነቱ ጸንቶ በመቆም መራርመስዋእትነት እንደከፈለ ሁሉ ወደፊትም በማንኛውም የከፋ ፈተናውስጥ ቢያልፍም ከጎንደሬ-አማራነቱ ሊያናውጸው የሚችልምንም አይነት ምድራዊ ሃይል ያለመኖሩን ነው። ምክንያቱምወልቃይት ጠገዴ አይደለም ለማንነቱና ለዕርስቱ፤ አምነውለተጠጉትም አንገት እንደማያስደፋ ትግራውያን ያውቃሉ!ታዲያ ወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ማነው?“በአፍ የመጣን በአፍ፣ በመጣፍ የመጣን በመጣፍ” መመለስየቀደሙ አባቶቻችን ስርዓትና ብሂል በመሆኑና ታሪካዊጠላቶቻችንም እንደ አመጣጣቸው መመለስ ተገቢ በመሆኑህወሃት በተላላኪዎቹ በኩል በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብመካከል ሊዘራ የሞከረውን እንክርዳድና በኢትዮጵያ ህዝብናበታሪካችን ላይ ሊፈጠር የታሰብውን ብዥታ ለማጥራት ሲባልናለታሪክም ምስክር ይሆን ዘንድ “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብማነው?” የሚለውን ጥያቄ በአጭሩ እንደሚከተለው ስንመልስጥልቁንና ተነግሮ የማይጠገበውን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምትታሪክ ለታሪክ ፀሃፊዎችና ለባለሙያዎች በመተው ነው።1. የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ እንደ ማንኛውምየሰሜኑ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሁሉ የአካባቢውን ስያሜበመውሰድ የእራሱ መጠሪያ አድርጎ ኖሯል። ለምሳሌየጎንደሬ ዘሩ ምንድነው? የሚኖርበት አካባቢ ስያሜ ማንይባላል? የጎጃሜውስ? የወሎዬው? የጋይንቴው?የምንጃሬው? የስሜንኛው? … ወዘተ ለመሆኑ እነዚህወገኖቻችን እራሳቸውን ሲጥሩ “እኛ ማነን” ይላሉ? እኛስእነርሱን እነማን ናቸው እንላለን? ጎንደሬውን – ጎንደሬ ፤ጎጃሜውን – ጎጃሜ ፤ ወሎዬውን – ወሎዬ፣ደብረታቦሬውን – ደብረታቦሬ፤ ጋይንቴውን – ጋይንቴ፤ስሜንኛውን – ስሜንኛ፤ በለሴውን – በለሴ፣ ወግሬውን –ወገሬ፣ ቋረኛውን – ቋሬ …. ወዘተ እያልን ወልቃይቴውን –ወልቃይቴ፣ ጠገድቼውን – ጠገድቼ፣ ጠለምቴውን –ጠለምቴ አላልንምን? እንላለን እንጂ!2. ታዲያ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ አባቱ ማነው?የዘር ሐረጉስ ከየት ይመዘዛል ቢሉ?ወልቃይት የሚለው ስም ከስር መሰረቱ የአማራ መስራችአባት የሚባለው የተጠቀሰበት አገር ነው። አማራውከወልቃይት ወደ ጠለምት ከዚያም ወደ ላኮ መልዛ(የዛሬው ወሎ) እያለ ሌላውን አካባቢ እያስፋፋ እስከሞቃዲሾ ተጉዞ ሃገር ያቀና ታላቅ ነገድ ያረፈበት መሆኑታሪክ ሁሌም ይመሰክራል። ወልቃይት ጠገዴ አማራየሆነው ዛሬ ትግሬ ሊያደርጉት እንደሚታትሩት በተዘዋዋሪሳይሆን የአማራ አባትና ግንድ በመሆን ነው። ለዚህ ፅሁፍበሚስማማ መልኩ ታሪካዊ ማስረጃዎችን እንመልከት።አለቃ ታዬ ወልደማርያም የተባሉ ሊቅና የተመሰከረላቸውታሪክ ፀሃፊ “የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ” በተባለው ዝነኛመፅሃፋቸው በገፅ 16 ላይ እንዲህ ፅፈዋል። “ከለውከሳባ ወደ ምዕራብ ወደ ደቡብ ያለ ያማራ የወልቃይትየጠገዴ አባት ነው። ከእነዚህም የኢትዮጵስ ልጆችየወንድማማቾቹ ነገድ ህዝብ ሁሉ በመልካቸውናበቁርበታቸው ይመሳሰላሉ። እኒህም ህዝብ የያዙት አገርበጥቅሉ ባባታቸው ስም ኢትዮጵያ ተብሎ ይጠራል።”በመቀጠልም የአማራው አባት አስገዴ ግንዱ ከወልቃይትጠገዴ አርማጭሆ ከዚያም እያደገና እየሰፋ አማራ ሳይንትድረስ የደረስ መሆኑን ገልጸው ጽፈዋል።አቶ አማረ አፈለ “ደም አይፍሰስ በቃ የህወሃት ማኒፌስቶያብቃ!” በሚለው መፅሐፋቸው በገጽ 27 ታሪካዊምስክርነታቸውን እንደሚከተለው አስፍረዋል።“ከተከዜ ጀምሮ ወደ ደቡብ እስከ ሸላሎ በተዘረጋው ምድርላይ ያሉት ወረዳዎች ሕዝቡ አፍ መፍቻ ቋንቋው አማርኛነው። ከትግራይ ጋር በተከዜ ወንዝ ድልድይነት ጎረቤትስለሆነ ወዲያና ወዲህ ማዶ ያለው የዐማራና የትግራይቋንቋ ቃላት ቢያንስ 80 በመቶ ተመሳሳይ በመሆናቸውመናገሩ አዳጋች አይሆንባቸውም። ይልቁንም የወልቃይትጠገዴና ጠለምት መዘጋዎች ጥጥ ስለሚያመርት ብዙየትግራይ ተወላጆች በጥጥ ለቀማ ወቅት በየዓመቱወደነዚህ መዘጋዎች ይመጣሉ። ዐማሮች ከእነርሱ ጋርለመግባባት ሲሉ ትግርኛውን ይጠቀሙበታል። ከእንግዶችመካከል ሀገሬውን አግብተው የሚቀሩም አይጠፉም።ለዚህም ወደ ኋላ መለስ ብለን ታሪክ ስንመረምርወልቃይት ጠገዴና ጠለምት በአክሱም፤ በላስታው በሽዋሆነ በጎንደር ዘመነ መንግሥት አንድም ግዜ የትግራይግዛት አካል ወይም ገባር የሆነበት የታሪክ ወቅት የለም።ይህን እውነት ለመረዳት ከጎንደር ዘመነ መንግሥት በፊትጀምሮ 20ኛ ምዕተ ዓመት ሁለተኛ አጋማሽ ድረስ የታወቁየውጭ ሀገር ጉብኝዎችና ታሪክ ፀሐፊዎች በተለያዩ ክፍለዘመናት ኢትዮጵያን እየተዘዋወሩ ካዩ በኋላ ስለብሔረስቦችና ስለ አስተዳደር ክፍሎች የተውልንጹሑፎችና ካርታዎች ህያው የታሪክ ማስረጃዎች ናቸው።”“ለአብነት ያህል ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ፤ ጅምስ ብሩስ፤ዶክተር ሚካኤል ረሥል፤ ማንስፊልድ ፓርኪንስ፤ ስቨንረንሰንወዘተ…….የተባሉ ታዋቂ ተመራማሪዎች ለትውልድያበረከቷቸውን መጻሕፍት መመልከት ይቻላል። ይልቁስየኢጣሊያን መንግሥት ኢትዮጵያን በ1928 ዓ/ምከመውረሩ በፊት በጐንደር ከተማና በሌሎች ከተሞችበከፈታቸው የቆንስል ቢሮዎች አማካይነት ባካሄደው ሰፊየኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ጥናት ባወጣው አስተዳደርመዋቅር ትግራይ ከኤርትራ ጋር ሲደርብ ጠገዴንናጠለምትን የአማራ ክልል በማድረግ ትግሬ አለመሆናቸውንአረጋግጧል።”