አዊ ብሄረሰብ ዞን

አዊ ዞን ለማስተካከል

➡ የዞኑ ዋና ከተማ፡- እንጅባራ

➡ የዞኑ ዋና ከተማ ከክልሉ ዋና ከተማ ያለውርቀት-122 ኪ.ሜ

➡ የወረዳዎች ብዛት፡- 9

  1. አንካሻ ጓጉሣ
  2. ባንጃ ሽኩዳድ
  3. ጓጉሣ ሽኩዳድ
  4. ፋግታ ለኮማ
  5. ዳንግላ ወረዳ
  6. ጃዊ ወረዳ
  7. ጓንጓ ወረዳ
  8. ዚገም ወረዳ
  9. አዘና ወረዳ
➡ የከተማ አስተዳደሮች 

ብዛት፡- 5

➡ የቀበሌዎች ብዛት፡-201

  • የገጠር፡-180
  • የከተማ፡- 23

➡ በዞኑ ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ብዛት፡-1,058,289

  1. ወንድ=916,015
  2. ሴት=142,274

➡ የወረዳው ስም የወረዳው ዋና ከተማ

  1. አንካሻ ጓጉሣ - አገው ግምጃ ቤት
  2. ባንጃ ሽኩዳድ - እንጅባራ
  3. ጓጉሣ ሽኩዳድ - ቲሊሊ
  4. ፋግታ ለኮማ - አዲስ ቅዳም
  5. ዳንግላ ወረዳ - ዳንግላ
  6. ጃዊ ወረዳ - ፈንድቃ
  7. ጓንጓ ወረዳ - ቻግኒ
  8. ዚገም ወረዳ - ቅላጅ
  9. አዘና/አዮ ወረዳ - አዘና

የአገው ሕዝብ አሁን በሚገኝባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ራሱን የሚገልጸው  አዊ ፡ኽምራ፡ቅማንት ፡ብሊን በሚሉ አካባቢያዊ መጠሪያዎች ነው ! ለማስተካከል

የስያሜው እድገት ከራሳቸው ወይም በጋራ  ከሚገኝ ማህበረሰብ ክፍሎች ተጨማሪ ቋንቋ የተዋሱት  ነው ለማስተካከል

✓አዊ ማለት አገው ማለት ነው ፡የቃሉ መነሻና ምንጭ የራሱ ቋንቋ አገውኛ ነው ሌሎችንም ራሱንም  አገው ለማለት ና ለመግለጽ ይህንኑ ቃል ይጠቀማል። ለማስተካከል

ትርጉሙ በአዊኛ ብራሃን ማለት ነው

✓ ኽምራ ማለት አገው ማለት ነው የቃሉ መነሻና ምንጭ የራሱ ቋንቋ አገውኛ ነው ፡ሌሎቹንም ራሱንም  አገው ለማለት ይኸንኑ ቃል ይጠቀማል። ለማስተካከል

✓ቅማንት ማለት የቤተሰብ ውቅር  አሰያየም ወይም የባሕላዊ ሃይማኖት ማህበረሰባዊ ልየታ ሲሆን የቃሉ መነሻና ምንጭ  አማርኛ ነው ፡  ቃሉን የሚጠቀሙት   የኦርቶዶክስ ክርስትያን ተከታዬች ሲሆኑ  ክርስትናም ይሁን ይሁዲ እምነት የማይከተሉትን  ቀደምት አገዎችን ክርስትያን አማሮች የሚገልጹበት ስያሜ ነው ። ለማስተካከል

✓ብሊን ማለት አገው  ማለት ነው ፡የቃሉ መነሻና ምንጭ የራሱ አገውኛ ቋንቋ፡የቤላ ትውፊትና በጋራ ካሉት የሳሆ  ቋንቋ ተናጋሪዎች የተወሰደ ሲሆን አገዎች ራሳቸውንና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ደግሞ አገዎችን ለመግለጽ ይጠቀሙበታል። ለማስተካከል

የአገው ታሪክ ለማስተካከል

እማዱክ ታሪክመግቢያአገው ምድር (አዊ ላጜታ) በሀገሪቱ ስርዓት አዊ ብሄ/አሰ/ዞንእየተባለ የሚጠራው አካባቢ ሰው ያልነበረበት ፣ጥቅጥቅ ያለ ጫካበዱር አራዊት የተሞላ ፣ ንፁህ የአየር ንብረት ለም አፈር ፣በቂ ውሃምቹ መልካአ ምድራዊ አቀማመጥ፣ የጫካ ማር ያለበት ጠፍእንደነበረ አፋአዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ ይሁን እንጂ የዚህ ቦታስያሜ የተሠጠው በአካባቢው በቀዳሚነት በሰፈሩት ሰባቱ አገውወንድማማቾች መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አገው ምድርእየተባለ የሚጠራው ቦታ በመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎች ሲሰየም ክልሉ(ወስኑ እስከ የት እንደነበር በትክክል መግለፅ ባይቻልም ከአሁኑ አዊብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ስር ካሉ ወረዳዎች በላይ እንደነበርእንዲሁም በምስራቅ ጎጃምና ደ/ጎንደር አካባቢ በአዊኛ ቋንቋየሚጠሩ አካባቢዎች (ቦታዎች )መኖራቸው ለብሄ/አስ/ዞን ወስንናስፋት ዋነኛ እማኞችለምሳሌ፡- ድኩል ካን ፣ዳድ ዩሃንስ (ምስ/ጎጃም )ቢዝራ ካኒ (ጎንደር)ጻና (ጣና) የሚባሉት ተጠቃሽ ናቸውሰባት ቤት አገው (ላጜታ አዊ)የተጠናከረና የተደራጀ መረጀ ባይኖርም በአፈ ታሪክ ደረጃ ከተለያዩአባቶችና ታሪክ አዋቂዎች የተገኙ መረጃዎች (oral sources)እንደሚጠቁመን የእስራኤል ደም ወገን የሆነው ንጉስ ሰለሞን የልጅኩሳ ከቀዳማዊ ሚኒሊክ ጋር ታቦተ ፅዮንን ከእየሩሳሌም ይዘውከመጡ በኋላ ንጉስ ኩሳ ሰቆጣ አካባቢ ትዳር መስርቶ በመኖርአዲልን ወለዱ ፣አዲል ደግሞ እና አንከሻ፣ባጃ፣መተከል፣አዘና፣ዚገም፣ኳኩራና ጫራን ወለዱ እነዚህ ወንድማማቾችከአካባቢያቸው ወደ ተለያዩ ቦታ እየተዘዋወሩ ዱር አራዊትን በማደንአዘውትረው ሲኖሩ ኑሮን ለማሸነፍ ፣ህይወትን በተሻለ መንገድለመምራት ከተፈጥሮና አካባቢ ጋር መታገል ግድ ይላል ፡፡ ካልሆነምአካባቢን ለቆ የተሻለ አካባቢ ፍለጋ መኳተን አሁንም በአንዳንድአካባቢዎች የሚስተዋል ተግባር ነው ፡፡ ስለሆነም ስባቱ አገዎችበአንድ ተሰማርተው በወቅቱ ውድና ተፈላጊ የሆኑ የዱር አራዊትማለትም የዝሆን ጥርስ ፣ጥርኝ ፣ዝባድና የመሳሰሉትን ፍለጋ ሲጓዙየትውልድ ቦታቸውን ስቆጣ ለቀው አሁን እንጅባራ እየተባለ ወደሚጠራው አካባቢ (ከሰንግ ይባል )ነበር ደርሰው አሁንም በአዊኛ“አንጉች ካና” ይባላል ፡፡ አካባቢው ምንም ሰው የሌለበት ፣በቂ የሆነየዱር አራዊትና ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ፣የዱር ማር ያለበት ፣ምቹመልካዓ ምድራዊ አቀማመጥና ሰላም የሰፈነበት ቦታ ሆኖበማግኘታቸው በአካባው ሁኔታና ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ በመማረክለሰባት ወራት ያህል የዱር አራዊትን በማደን ቆይተው ሰባቱምወንድማማቾች ወደ ቤተሰቦቻቸው (ሰቆጣ )በመመለስ፣ለቤተሰቦቻቸውም ተመላልሰው ስለተመለከቱት አካባቢመልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ ፣ለኑሮ ምቹና ተስማሚ የአየር ንብረት፣በውስጡ ያሉ የዱር አራዊትና ተፈጥሮአዊ ገፅታ ሲገልፁላቸውቤተሰቦቻቸውም በሀሳባቸው ተስማምተው ለጥያቄአቸው አወንታዊምላሽ በመስጠት መልካም ፈቃዳቸውን መርቀው ልጡንገመድ፣ባዳውን ዘመድ ያድርላችሁ ሲሉ ሰባቱ ወንድማማቾችሚስቶቻቸውን ልጆቻቸውን ከብቶቻቸውን እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸውአገልጋያቸው ትሆን ዘንድ የተላከቸውን አዱክን ጨምረው ጎዞቸውንወደ ተመለከቱት አካባቢ ቀጠሉ፡፡ ወደ አዲሱ አካባቢ ደርሰውበታላቃቸው አንከሻ መሪነት ቦታ ሲከፋፈሉ አንከሻና ባንጃ አማካኝ የሆነቦታ ሲይዙ ኳክራን በምስራቅ ፣ጫራን በምዕራብ፣ዚገም፣መተከልናአዘና በስተደቡብ እንዲቀመጡ አድርገዋል፡፡ አማካይ በሆነ አቅጣጫአንከሻና ባንጃ በመሆን አዱክ ታገለግላቸው ነበር ፡፡ በተጨማሪምለሌሎች ወንድማማቾች በመሆኑ እንደ መገናኛ ይጠቀሙበት ነበርይላሉ የታሪክ አባቶች ፡፡አዱክ ከሰባቱ ወንድማማቾች ጋር በአገልጋይነት ከሰቆጣ የተላከችው አዱክ ስትቅልባቸውና ስታገለግላቸው ኑራ አምስቱ በተልያዩ አቅጣጫ ቦታቦታቸውን ሲይዙ እሷ ግን በታላቃቸው አንከሻና ባንጃ መካከል በመሆንእንድትኖር ተደርጓል፡፡ በመሆኑም አገልጋያቸው አዱክ በዕድሜእየገፋች ለስራ ጉልበቷ እየደከመ ሲሄድ እንደገና መጦር ግድ ሆነባት፡፡ በሁለቱ ወንድማማቾች ትርዳና ትጦር ጀመር ይህም ሲሆን አንከሻበደቡብ አብልቶ አጠጥቶ አጥቦና አልብሶ ድንበራቸው በሆነ ቦታ ላይፀሐይ ሲሞቅ ብርዱም ሲለቅ አስቀምጦ ሲሄድ ፣ባንጃም በተራውበመውሰድ ቤቱ አሰንብቶ ለተረኛው ሲሰጥ እንደቤቱ አብልቶናአጠጥቶ በጥዋቱ ፀሐይ ሰትታይ ከቦተዉ የደርሣት ነበር በመሆኑምአዱክ በጥዋቱ ቁርና በቀጥር ሙቀት ይፈራረቀባት ስለነበር አንከሻንናባንጃን ትመርቃቸው ነበር ይላሉ አባቶች(አባሆይ ዘሩ አለሙ)አንከሻን /ክምምባ ኹ ክም አንካ እይምኽ /እስከ ማታ ብላ ባንጃንስግላ ቻንቑዋ ስግላ አንካ ኹ /የማለዳ እንጀራ ብላ/እማ አዱክየተለያዩ መላምቶች “አዱክ” የሰባቱ አገው እናት ናት እየተባለ ሲወራይስተዋላል ፡፡ ስለሆነም ከተለያዩ አባቶች ታሪክ አዋቂዎችና የአካባቢነዋሪዎች የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው አዱክ የሰባቱ አገውወንድማማቾች “ ወላጅ እናት ” አይደለችም ነገር ግን እነሱ ወደ ዚህአካባቢ ሲመጡ ከቤተሰቦቻቸው የተላከች አገልጋያቸው(ሞግዚታቸው ናት ) የሰባቱ ወንድማማቾች እናት ማናት ? ሲባልአዱክ ይባላል ይህምየሆነበት ምክንያት1. የብረሄረሰቡ ባህል ፣ ቋንቋና ወግ መሰረት በዕድሜ ትልቅ የሆነችእህት ፣አክስት ፣የእንጀራ እናት ወይም አሳዳጊ2. በኢትዮጴያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት መሰረትየክርስትና እናት3. በመኳንት ወይም መሳፍንት ቤተሰብ ቤት ውስጥ የምታገለግል፣ሴት የልጅ ጠባቂ ፣ቀላቢ እና ተንከባካቢ እንደ ወላጅ እናት “እናት”ተብላ እንደምትጠራ ይታወቃል ፡፡ ስለሆነም አዱክ የሰባቱ አዊእናታቸው ሳትሆን ቀላቢያቸውና አገልጋያቸው እንዲሁም የልጆቻቸውሞግዚታቸው በመሆኗ እናት ተብላ ትጠራለች ፡፡ አዱክ በአንዳንድአካባቢዎች እማ-አዱክ ተብሎ ስሟ ሲጠራ ይስተዋላል፡፡ ይህ የሆነው“እማ” የሚለው ቅፅል ስም በዕድሜ ትልቅ ለሆኑ ሴቶችና እናቶችየሚሰጥ የክብር ስም በመሆኑ አዱክ የሰባት አገዋች አገልጋያቸውናየልጆቻቸው ሞግዚትም ስለሆነች እማ አዱክ እየተባለች በክብርስትጠራ፣(በማ/ሰቡ ባህል ፣ወግ፣ቋንቋ የእምነት ስርዓት መሰረት፣ታላቆችን በስም ብቻ አይጠሩም ፣በአክብሮት፣በትህትናና በማዕረግስማቸው ይጠራሉ።የአዱክ መቃብርበኳሪ ጎኻና ቀበሌ ፣በተርዬ ታራረ ዙሪያው በጥድ ዛፍ የተከበበካችንቲ ተራራ (አለት በስተ ደቡብ ፣የእማ አዱክ መቃብር ስፍራይገኛል፡፡ ምክንያቱም የድንጋይ ቁልል ይታያል፡፡ የመቃብር ቦታ እዚህለመሆኑ የሚያመለክቱ መረጃዎች1. እማ አዱክን አንከሻና ባንጃ ይጦሯት ስለነበረና ይህ ቦታ ደግሞየሁለቱ ወሰን (ድንበር መሆኑ )2. አንከሻና ባንጃ በሚጦሯት ጊዜ የሚረካከቡበት ቦታ ስለነበር3. ይህ ቦታ ለሰባቱም ወንድማማቾች አማካይ (መገናኛ) በመሆኑበታላቆች ምክርና መሪነት መመሪያቸው4. በወቅቱ በቅርብ ርቀት (አካባቢ ቤተ ቤተክርስቲያን አለመኖርተጠቃሽ አፋዊ መረጃዎች ናቸው ፡፡ በሰሜን የባንጃ በአሁኑ ወረዳችንፋግታ ለኮማ ፣በስተ ደቡብ የአንከሻ (በሁኑ ባንጃ ወረዳ ) ክልል፣ከአ/ቅዳም ከተማ ወደ ኮሰበር በሚወስደው ------መንገድ ፣አሮጌእንጅባራ ወይም በድሮ አጠራር ሰፈር ገቢያ እንዳደረስን ወደ ቀኝበኩል በመታጠፍ ቀጥ ብለን ብንሄድ በግራና በቀኝ በጥድ ዛፍየተከበበ ልዩና ማራኪ የሆነ ታሪካዊ ቦታን እናገኛለን፡፡ ይህ ቦታ- በቀደምት አዱክን አንከሻና ባንጃ የሚረካከቡበት ሲሆን- ዙሮ ዙሮ ቤት ፣ኑሮ ኑሮ ሞት እንዳሉ በኋላም የእማዱክ መቃብርስፍራ ነው ፡፡እዚህ ቦታ መሀል ለመሀል ሰፊ የሆነ ጎዳ/መንገድ ከአ/ቅዳም ናእንጅባራ ወደ ኳሪ ጎኻና የሚያደርስ ሲኖረው በዚህ መንገድ የሚያልፍማንኛውም ሰው እንደሌለው አካባቢ ምንገድ አቋርጦ አያልፍም /አይሄድም ልዩ የሆነ ባህላዊ ታሪካዊ ስርዓት ያለማንም መካሪነትናትዕዛዝ ሲፈፀም/ሲከናወን ይታያል፡፡ ይኸውም መንገደኛው እማዱክመቃርብ ሊደርስ የተወሰነ ርቀት ሲቀረው በቀኝ እጁ ድንጋይ ይዞመጣል አያያዙም እንደ ማንኛውም ተራ ውርወራ ሳይሆን ልክ በቀኝእጁ ይዞ በትክሻው ቀጥታ ቦታው ላይ ሲደርስ በቀኝ በኩል ካለውየድንጋይ ክምር ይጠለዋል ፡፡ በመቀጠልም እዚች ቦታ ላይ ቁጭ ብሎያርፋል ፡፡ ይህ የሚካሄደው ምን ጊዜ በቀኝ በኩል ባለው ስፍራ ነው ፡፡ለምን ቢሉ- በቀኝ እጅ መያዛቸው ቀኝ እጅ ሁልጊዜም ገር ፣ቀናና መልካምዕድልና ምኞች በመሆኑ- ከቦታው ሲደርሱ ማረፊያ መቀመጫቸው ከእናታቸው በረከትለመሳትፍ- ድንጋይ መጣል እረም ማውጣት ለመቃብር መታሰቢያነት ይህምበማ/ሰብ ወግና ባህል መሰረት ሰው ሲሞት እልቅሶ ቦታ ላይ ሲደርሱፊት ይጠረጋል ፣ቁጭ ብለው መነሳት፣ለወደፊቱም ለነፍስ መልካምመመኘት የተለመደ ስርዓት ነው ፡፡ የተለያዩ የፅሑፍ መረጃዎችን አፋዊመረጃዎችን በመጠቀም መረጃዎችን በመሰብስብ ፅሑፉን ማጠናከርተችሏል ፡፡ማጠቃለያወረዳችን ይህንና የመሳሰሉ ጥንታዊና ታሪካዊ ህዝብ ባለቤት ልዩ ልዩጥንታዊና ባህላዊ ቅርሶች መገኛ የተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ መስህብስፍራዎች ባለቤት መሆኑን መገለጫ ለሆነው ባህላችንና ቅርሶቻችንትኩረት ሰጥተን መጠበቅ መንከባከብና ተጠብቀው ለትውልድየሚተላለፉበትን መንገድ ማመቻቸት የሁላችንም የህሊና ግዴታ ሊሆንይገባናል ፡፡

የአገው ታሪክ ለማስተካከል

የአገው ታሪክ እጅግ ሰፊ ነው፡፡ባለታሪክ ህዝብ አሁን ሰዓት በአስተዳደር ችግር ወደ ልመነ ወጦዋል

  • የላስታ _ ዋግ ( ዛጔ ) ነገሥታት ስም ዝርዝርና የነገሱበት ዘመን

1. መራ ተክለ ሃይማኖት ...920 _ 933 አ.ም ...13 አመት

2. ስቡሀይ ( ድልነአድ )...933 _ 943 አ.ም ...10 አመት

3. መይራሪ ... 943 _ 958 አ.ም ...15 አመት

4. ሀርቦይ ( ሀረየነ እግዚእ ) ...958 _ 966 አ.ም ...8 አመት

5. መንግሥትነ ይትባረክ...966 _ 973 አ.ም ...7 አመት

6. ይእቀብከ እግዚእ...973 _ 983 አ.ም...10 አመት

7. ዜና ጴጥሮስ ...983 _ 989 አ.ም...6 አመት

8. ባሕር ሰፍ...989 _ 1003 አ.ም....14 አመት

9. ጠጠውድም ( ፀር አሰግድ )...1003 _ 1013 አ.ም ...10አመት

10. ጃን ስዩም ( አኩቴት ) ...1013 _ 1033 አ.ም...20 አመት

11. በእምት ( ግርማ ስዩም )...1033 _ 1053 አ.ም ...20 አመት

12. ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ...1053 _ 1093 አ.ም...40 12.ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ...1053 _ 1093 አ.ም...40 አመት

13. ቅዱስ ገብረ ማርያም...1093 _ 1133 አ.ም...40 አመት

14. ቅዱስ ላሊበላ...1133 _ 1173 አ.ም...40አመት

15. ነአኩቶ ለአብ ...1173 _ 1213 አ.ም...40 አመት

16. ይትባረክ ... 1213 _ 1253 አ.ም...40 አመት

  • የነገሱበት አመት ድምር 333 ይሆናል።

@ ምንጭ # የአገው ህዝቦች ና የዛጉዌ ስርወ መንግስት ታሪክ

  • በ ዶ/ ር አያሌው ሲሳይ

@ ከገፅ 92 የተወሰደ።