ዓለማየሁ ቴዎድሮስ

ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ እና የወይዘሮ ጥሩወርቅ ውቤ ልጅ ነበር።በ1860 ዓ.ም አፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር ባደረጉትጦርነት ልጃቸው ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ወደ እንግሊዝሀገር ተወስዶ ነበር፡፡ በዛሬው የኛ አምዳችንም የዚህን ልዑልባዕድ ሀገር ኑሮ ልናስቃኛችሁ ወደድን፡፡ልዑል አለማየሁ ሚያዚያ 5 ቀን 1853 ዓ.ም በደብተረታቦር ከተማ ነበር ውልደቱ፡፡ በልዑሉ ውልደት የተደሰቱትአፄ ቴዎድሮስም በእለቱ መድፍ ያስተኮሱ ሲሆን 500ያህል እስረኞችንም ፈትተዋል፡፡ ከልዑሉ ጋር ሲጫወቱመዋል አፄውን እጅግ የሚያስደስት ነገር ነበር፡፡ ተናደው እናተበሳጭተው ከነበር እንኳን አለማየሁን ታቅፈው ሲስሙንዴታቸው ይበርድ ነበር ይባላል፡፡ልዑል አለማየሁ እንግሊዞች እጅ ከገባ ቡሀላ ከእድሜውለጋነት የተነሳ የሚጠብቀው እና የሚንከባከበው ሰውሊኖር ግድ ነበር፡፡ ይህንን የተረዳው ጀነራል ናፔር ካፕቴንስፒዲ የተባለን ሰው የአለማየሁ ጠባቂ እንዲሆን መደበው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ካፕቴኑ የአማርኛ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገሩ ነበር፡፡ በተጨማሪም አለቃ ዝርዓት እናአቶ ገብረመድህን የተባሉ ሁለት ኢትዮጵዊያን ሞዚቶች እናአጫዋቾች¬ ተመረጡለት፡፡አለማየሁ ከጠባቂው ስፒዲ ጋር ፌሬዝ በተባለችው መርከብተሳፍሮ በ1860 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝ አቀና፡፡ በመርከቢቱላይ በነበራቸውም ቆይታ ስፒዲ እና አለማሁ እጅግ የጠበቀወዳጅነትን መስርተው ነበር፡፡ ስፒዲ በሄደበት ቦታ ሁሉአለማየሁን ማስከተል ያዘወትር ነበር፡፡ ይህንን የሁለቱንፍቅር ያየው ጀነራል ናፒየርም ኢትዮጵያውያን ሞግዚቶቹወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ይልቁንም የአለማየሁንሀላፊነት ሙሉ በሙሉ ካፕቴን ስፒዲ እንዲረከብ ስለወሰነሁለቱ ሞግዚቶች ጉዞው ተጠናቆ እንግሊዝ ሀገር ሳይደርሱከስዊዝ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ፡፡ ምንምእንኳን የእንግሊዛውያኑ የታሪክ ድርሳናት ይህንን ቢሉምልዑሉ ኢትዮጵያውያን ሞግዚቶቹን በተባለው መጠንአምርሮ ይጠላቸው እና ባያቸውም ቁጥር በብስጭት ያለቅስ እንደነበር ማረጋገጫ የለንም፡፡ከሶስት ወራት የመክረብ ላይ ጉዞ በኃላ አለማየሁ እንግሊዝሀገር ደረሰ፡፡ እዛ አንደደረሰም የወቅቱ የእንግሊዝ ንግስትከነበረችው ንግስት ቪክቶሪያ ጋር ተገናኘ፡፡ ንግስቲቱምልዑሉ የፈለገው እና ያሻው ይደረግለት ዘንድ ቀጭንትዕዛዝ አስተላለፈች፡፡ ልዑሉ በመቀደላ የነበረውንእልቂት በመጠኑም ቢሆን በማየቱ እና የአባቱ እና የእናቱተከታታይ ሞትም በልጅ አዕምሮው ሊቀበለው ከሚችውበላይ ስለነበር እጅግ ታውኮ እንደነበር በተደጋጋሚ ተፅፎእናገኛለን፡፡ አንድ እንግሊዝ ሀገር ውስጥ በሚገኝ ሙዚየምውስጥ ባለ የንግስት ቪክቶሪያ የእለት ማስወሻ ላይምንግስቲቱ፡ “ምስኪኑ ልጅ አሁንም ፍርሀቱ አለቀቀውም፡፡መቅደላ የነበረው እልቂት እና የአባቱን ሞት ስላየ ያ ነገርበአዕምሮው ይመጣበታል፡፡ “ የሚል ቃል ፅፋ እናገኛለን፡፡ልዑሉ እንግሊዝ ሀገር ከደረሰ በኃላ ጠባቂው የነበረውካፕቴን ስፒዲ የእንግሊዘኛ ቋንቋን ያስተምረው ጀመር፡፡ ንግስቲቱም የልዑሉን ሁኔታ በቅርበት ትከታተል ነበር፡፡ስፒዲ ልጁን እንዳይጎዳው በማሰብም በስፒዲ ላይ የልዑሉንጉዳይ በቅርበት የሚከታተል ተቆጣጣሪ አስቀምጠውበትነበር ይባላል፡፡አንድ ግዜ ንግስት ቪክቶሪያ ስለ ልዑሉ በእለት ውሎመመዝገቢያዋ ላይ ከመዘገበችው መሀል “ልጁ ጨዋእና ውብ ልጅ ነው፡፡ ኬክ መብላት ደግሞ ይወዳል፡፡ የሰጠሁትንም ኬክ ሁሉ ጨርሶ በላ፡፡” የሚል አረፍተነገር ተፅፎ እናገኛለን፡፡ ንግስቲቱ በተደጋጋሚ ለዚህ እናትለሌለው ልጅ እናቱ እኔ ነኝ ስትል ትደመጣለች፡፡ ለልዑሉምየተለየ አክብሮት እና ፍቅር ፤ ልዩ ትኩረትም እንደነበራትድርሳናት ዘግበውታል፡፡ምንም እንኳን ከንግስቲቱ ጋር የነበራቸው ወዳጅነትከግዜ ወደ ግዜ እየበረታ ቢመጣም ከሀገሩ ሲወጣ አብሮትየነበረውን ካፕቴን ስፒዲን ግን ለአፍታም አልዘነጋውምነበር፡፡ በየትኘውም ስፍራ ሲሄድ ስፒዲ አብሮት እንዲሆንይፈልጋል፡፡ ግብዣም ሲሄድ ሆነ ከልዑላን ልጆች ጋርእንዲጫወት ሲጋበዝ ስፒዲን ትቶ መሄድ አይሆንለትም፡፡ ቤተ-መንግስት ሲገባ እንኳን ስፒዲን አስከትሎ ነው፡፡ስፒዲ እና አለማየሁ አብረው ይበላሉ አብረውም ደግሞይተኛሉ፡፡ አለማየሁን ለብቻው ማሳደግ የከበደው ስፒዲልጁን በማሳደግ ትረዳው ዘንድ ሚስት ለማግባት ወሰነ፡፡ከዛም ወ/ሮ ኮታንን አገኘ እና አገባት፡፡ አለማየሁ እና ወ/ሮኮታንም ለመዋደድ ግዜ አልወሰደባቸውም ነበር፡፡በ1861 ዓ.ም ስፒዲ ህንድ ሀገር በምትገኝ አንዲት ከተማ አዛዥ ሆኖ ስለተሾመ የ8 ዓመቱን አለማየሁን እናሚስቱን ይዞ ወደዛው አቀና፡፡ በሄዱበት ሀገርም አለማየሁትምህርቱን መከታተሉን ቀጥሎ የነበረ ሲሆን ከመደበኛውትምህርት በዘለለም ፈረስ ግልቢያ እና ሌሎች ስፖርቶችንምያዘወትር ነበር፡፡ልዑሉ በዚህ አይነት ከቆየ በኃላ ቻንስለር ሮበርት ሉዊ ልዑሉየቀለም ትምህርት ላይ ከሚያዘወትር ይልቅ የወታደርትምህርት ቤት ገብቶ የፈረስ ውትድርናን እንዲማርመደረግ አለበት ሲሉ ያቀረቡት ሀሳብ የልዑሉን ህይወትእስከወዲያኛው የለወጠ ነበር፡፡ ይህም ሀሳብ ተቀባይነትንስላገኘ አለማየሁን ከስፒዲ ነጥሎ በመንግስት ቁጥጥርስር ለማድረግ እና የውትድርና ትምህርቱን እንዲከታተልተወሰነ፡፡ ይህ ውሳኔ ግን ለአለማየሁም ሆነ ለስፒዲ ከባድግዜ ነበር፡፡ ስፒዲ እና ሚስቱ አለማየሁን ላለመስጠትከባድ ትግልን አደረጉ፡፡ ነገር ግን ትግላቸው ውጤትንአላስገኘላቸውም፡፡ ይልቁኑም አለማየሁ ወደ እንግሊዝሀገር እንዲመለስ ተወሰነ፡፡ስፒዲም አለማየሁን ይዞ ወደ እንግሊዝ መጣ፡፡ የአለማየሁአዲሱ አስተማሪ እና ጠባቂ እንዲሁኑ የተመረጡትምበአስተማሪነታቸው የተመሰከረላቸው እና በደግነታቸውየታወቁት ቄስ ብሌክ ነበሩ፡፡ ንግስት ቪክቶሪያምየአለማየሁን እና የስፒዲን ፍቅር ያውቁ ስለነበር ሁለቱንቶሎ መነጣጠል አልፈለጉም፡፡ ይልቁኑም አለማየሁ ከቄስብሌክ ጋር እስኪላመድ ድረስ ስፒዲ አብሮት ይቆይ ስትልፈቀደች፡፡አዲሶቹ የአለማየሁ ጠባቂዎች አለማየሁ ስራ እንዲሰራወሰኑ፡፡ በወጣለትም ፈረቃ መሰረት በሳምንት ለ 31 ሰዓትተኩል ያህል ማንኛውንም አይነት ስራ እንዲሰራ ተወሰነ፡፡ የስፒዲ ሚስትም ይህንን በመቃወም ጠባቂው ለነበሩትበቢዶልፍ ደብዳቤ ላከች፡፡ ቢዶልፍም ለሉዊ አለማየሁአንዳንድ ግዜ እየሄደ ከስፒዲ ሚስት ጋር ግዜ እንዲያሳልፍሲሉ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ በትዕዛዙም መሰረት የስፒዲሚስት ከአለማየሁ ጋር እንድትውል ተፈቀደላት፡፡ ሚስቱምአብራ ውላ ያየችውን እንዲህ ስትል በደብዳቤ ገልጣለች፡“ማደጉን ቁመቱ አድጓል፡፡ መልኩ ግን ገርጥቷል፡፡ አካላቱምከስቷል፡፡ ዝምተኛ እና ጭምትም ሆኗል፡፡ ከወንዶች ልጆችጋር እንዳይገናኝ እና ከእኩዮቹም ጋር እንዳይገናኝ ተደርጓል፡፡ ውጪ እየወጣም እንዳይዘል ታግዷል፡፡ እየደጋገመም‘አብረውኝ የሚጫወቱ ልጆች አጣሁ፡፡ ቅዳሜ እና እሁድብቻ ከሁለት ልጆች ጋር አንድጫወት ይፈቀድልኛል፡፡ሊያጫውቱኝ የሚመጡትም እነዚህ ልጆች ሁልግዜ እነሱ ብቻ በመሆናቸው ተሰላችተናል፡፡ በሌላ ቀን ግን የሌሎችልጆችን እጅ አንኳን ጨብጬ አላውቅም’ ብሎኛል፡፡ ይህንን የመሰሉት ነገሮች ያበሳጩታል፡፡ እኔም ብሆንይህን የሚበሳጭበትን ጉዳይ ለማስተው ጓደኛ ልፈጥርለትአልቻልኩም፡፡ እየደጋገመ የነገረኝም ‘ወንዶች ልጆችእፈልጋለሁ፡፡ የበለጠ እንድንዛመድም እፈልጋለሁ’ እያለነው፡፡ በምግብ አበላሉ በኩልስ እንዴት ነህ ብዬ ብጠይቀው‘ምግብ አሁን አይበላልኝም፡፡ ምክንያቱም ውጪ ወጥቼስለማልዛለል እና ስለማልጫወት አይርበኝም፡፡ የምበላውበትንሹ ነው’ ብሎ መለሰልኝ፡፡ እኔ እንደማስበው አለማየሁደስተኛ እና በሚደረግለት የረካ ልጅ አይደለም፡፡”የስፒዲ ሚስት የፃፈችው ይህ ደብዳቤ ከንግስት ቪክቶሪያዘንድ ደረሰ፡፡ ንግስቲቱም ትንሹ ልዑል አብሮአቸውሊጫወት የሚችሉ ጓደኞች እንዲፈለጉለት አዘዘች፡፡እንደተባለውም ተደረገ፡፡1867 ዓ.ም አለማየሁ ወደ ራግቢ ትምህርት ቤት ተዛወረ፡፡ በዚህም ከቄስ ብሌክ ቤት ወጥቶ ወደ ሊው ዋርነር ቤትእንዲገባ ተደረገ፡፡ በዚህ ግን ደስተኛ ስላልነበር በቀጣዩ አመት ሚስተር ድራፐር ቤት እንዲኖር ተደረገ፡፡ ቄስብሌክም ካዩት የልዑሉ ባህሪ በመነሳት ልዑሉ ወታደርነትላይ ቢያተኩር የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ተናገሩ፡፡በዚህም ንግግር መሰረት የወታደር ትምህርት ቤት እንዲገባተደረገ፡፡በአንድ ወቅት አለማየሁ ወደ ሊድስ በመሄድ በሰር ራምሰንቤት ተቀምጦ በነበረበት ወቅት በመርዝ ተመረዘ። መርዙ ህዳር 5 ቀን 1872ዓ.ም ከጠዋቱ በ3 ሰዓት ከሩብ በተወለደ በ19 ዓመቱከዚህ አለም እንዲሰናት አደረገው፡፡ አስከሬኑም ዊንድሶርባለው የነገስታት መቀበርያ በክብር አረፈ፡፡ በመቃብሩምላይ “የሀበሻው ልዑል አለማየሁ” የሚል ፅሁፍ ሰፍሮበትእስካሁን በእንግሊዝ ሀገር ይገኛል፡፡

ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ በእንግላንድ