እሷ ትታቀፋለች
እሷ ትታቀፋለች
(20) የመሸባቸው መንገደኞች አለቃ ገብረሀና ቤት ምሽቱን ለማሳለፍ ይጠይቁና እንደ ባህሉ አለቃ “ቤት ለእንግዳ” ብለው ማደሪያ ይሰጧቸዋል። እንግዶቹም ፈረሶቻቸውን እደጅ አስረው ይገባሉ። አለቃንም «እባክዎ ፈረሶቹ እርቧቸዋልና ሳር ይስጡልን» ብለው ይጠይቃሉ። አለቃም «ምን ችግር አለ ታዲያ ከውጭ አጭጄ አመጣላቸዋለሁ» ይላሉ። ነገር ግን የአንዱ እንግዳ አይን ማዘንጊያ ላይ ሲቁለጨለጭ ያጤኑት አለቃ፤ ነገሩ ስላላማራቸው ማዘንጊያን ነይ እስቲ ተከተይኝ ይላሉ። እንግዶቹም«ለምን እሳቸውን (ማዘንጊያን) ያደክማሉ?» ብለው ይጠይቃሉ። አለቃም «አይደለም እኮ እንዲያው እኔ ሳጭድ እርሷ ትታቀፋለች ብዬ ነው» በማለት ስጋታቸውን በዘዴ ገለጹ።
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽፋይዳ መታወቂያልዩ:Searchውክፔዲያ ውይይት:ምንጭጌየአድዋ ጦርነትጥላሁን ገሠሠጂፕሲዎችአፈወርቅ ተክሌሥርዓተ ነጥቦችኢትዮጵያአማርኛሀጫሉሁንዴሳየአክሱም ሐውልትውይይት:ዋናው ገጽአበበ ቢቂላሚላኖላሊበላጀጎል ግንብኢትዮ ቴሌኮምኤችአይቪመጽሐፍ ቅዱስቅዱስ ያሬድአክሱምዓፄ ቴዎድሮስቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕትዳግማዊ ምኒልክአርሰናል የእግር ኳስ ክለብአውሮፓገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችማርያምሆሣዕና በዓልጉግል2ኛው ዓለማዊ ጦርነትየኦሎምፒክ ጨዋታዎችt8cq6ዘጠኙ ቅዱሳንየቅርጫት ኳስየጋብቻ ሥነ-ስርዓትእርዳታ:ይዞታ