አረቄ የሚለው ቃል ከበርካታ የመካከለኛው ምስራቅ የአልኮል መጠጥ ስያሜ ጋር ይመሳሰላል በአረብ araq ማለት የተጣራ ማለት ነው

አረቄ ማውጫ መሳሪያወች፣ ጣና ደሴቶች

አረቄ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ የአልኮል መጠጥ ነው።

አረቄ አወጣጥ ለማስተካከል

  1. የኢትዮጵያ አረቄ አዘገጃጀት በአጭሩ...

1ኛ• በበቂ ሁኔታ ደርቆ የተፈጨ እኩል ይዘት ያላቸው በቆሎ እና ብቅል ማዘጋጀት (ለምሳሌ አንድ ቁና ብቅል እና አንድ ቁና በቆሎ).2ኛ• ብቅሉን በእንስራ አድርጎ በላዩ ላይ ውሃ መሙላት።.3ኛ• በመቀጠልም የተፈጨውበቆሎ በዋድያት /በዝርግ እቃ/ አድርጎ በውሀ ከተንፈረፈረ በኋላ በማግስቱ በብረት ምጣድ ማንኮር።.4ኛ• በመቀጠልም በተዘጀውብቅል ላይ በሶስተኛው ቀን 1 እንስራ ውሃ ተጨምሮ እንኩሮው ይደረጋል።.5ኛ• ከዚህ በኋላ ቢያንስ በ6ኛ ወይም 7ኛ ወይም 10ኛ ቀኑ እንደየሠው የሥራ ባህል እየታየ አረቄውን ጥዶ ማውጣትይቻላል፡፡.6ኛ• አረቄውን ለማውጣት በእሳት ላይ የሚጣደውም እንስራ ሲሆን እንስራው ሲጣድም ጋደም /ዘንበል/ ብሎ ነው፡፡.7ኛ• እንስራው ሲጣድም ከቂጡበኩል የተጣመመ ሸምበቆ በእንስራው አንገት ላይ ይሰካና የእንስራው አፍ በጭቃ ይመረጋል፡፡ ሸምበቆው የተጣመመ የሚሆንበት ምክንያትም አረቄው ከእንስራው በተጣመመውሸንበቆ በኩል ወደ ኮዳው እንዲወርድ እንዲያግዝ ነው፡፡ በሌላ መልኩ እንስራው የሚመረግበት ምክንያትም የሚወጣው አረቄ የእንፋሎቱ ውጤት በመሆኑእንፋሎቱ እንዳይወጣና ቀዳዳ እንስራው አፉ ላይ እንዳይኖር በማሰብ ነው፡፡.8ኛ• በመቀጠልም በተጣደው እንስራ አንገት ላይ ጠማማው ሸምበቆ ከተደረገ በኋ በሸምበቆው አፍ እና በኮዳውአፋ የምትገባ ቀለም መሳይ ክፍት ቀጭን ሸንበቆ ከተደረገች በኋላ በጎራሽ /ዋድያት/ ዝርግ ሸክላ ኮዳው እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡ በመቀጠልም ከኮዳው አንገት እስኪደርስ ውሃበጎራሹ ውስጥ እንዲሞላ ያደርጋል፡፡ [ውሃ በጎራሽ ውስጥ የሚደረግበት ምክንያት ኮዳው እንዳይፈነዳ እና ውሃው ኮዳውን እንዲያቀዘቅዘው በማሰብነው፡፡ ከጎራሹ ውሃ የሚደረገውም የተወሰነ እሳት ከነደደ በኋላ ነው፡፡].9ኛ• በመቀጠልም እሳት በተደጋጋሚ እንዲነዱበት ከተደረገ በኋላ አረቄ ሁኖ ለመውጣት እና አንድ ኮዳ ለመሙላትቢያንስ 4 ስዓታትን ይፈጃል፡፡ እሳቱበተደጋጋሚ ከነደደ በኋላ በመጀመሪያ የማውጣው የኮዳው አረቄ ዋናው አረቄ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው አረቄ ግን ሳቢያ /መጠቅለያ/ ይባላል፡፡በዚህ መልኩ ቆንጆ የሃበሻ አረቄን ማዘጋጀት ይቻላል፡፡