ምልምሎች
ምልምሎች
(26) ለእንጦጦ ማርያም ይመስለኛል ጣይቱ ለመዘምራንነት ድምጸ መረዋ የሆኑ ስልቦችን ለአገልጋይነት ይሰጣሉ። እነዚህ መዘምራን ከአለቃ ጋር በምን እንደተጣሉ አይታወቅም። አለቃ እነሱን እናንተ ምልምሎች ይሏቸዋል። መዘምራኑም ምኒልክ ዘንድ ይከሳሉ ተሰደብን ብለው። አለቃም ተጠርተው ሲጠየቁ አልተሳደብኩም ይላሉ። ከዚያ ምን ብሎ ነው አለቃ የሰደባችሁ ይላሉ ምኒልክ። መዘምራኑ አፍረው ዝም ሲሉ አለቃ ምን ትላለህ ይሏቸዋል። አለቃም አልተሳደብኩም እቴጌ ጣይቱ ከአገልጋዮቻቸው መካከል መርጠው መልምለው ለእንጦጦ ማርያም ስለሰጡ ነው ምልምሎች ያልኩት አሉ። ምኒልክም ስቀው ዝም አሉ አሉ።
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽፋይዳ መታወቂያልዩ:Searchውክፔዲያ ውይይት:ምንጭጌየአድዋ ጦርነትጥላሁን ገሠሠጂፕሲዎችአፈወርቅ ተክሌሥርዓተ ነጥቦችኢትዮጵያአማርኛሀጫሉሁንዴሳየአክሱም ሐውልትውይይት:ዋናው ገጽአበበ ቢቂላሚላኖላሊበላጀጎል ግንብኢትዮ ቴሌኮምኤችአይቪመጽሐፍ ቅዱስቅዱስ ያሬድአክሱምዓፄ ቴዎድሮስቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕትዳግማዊ ምኒልክአርሰናል የእግር ኳስ ክለብአውሮፓገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችማርያምሆሣዕና በዓልጉግል2ኛው ዓለማዊ ጦርነትየኦሎምፒክ ጨዋታዎችt8cq6ዘጠኙ ቅዱሳንየቅርጫት ኳስየጋብቻ ሥነ-ስርዓትእርዳታ:ይዞታ