መዓትኸሩሬ፣ ፬ አመነምሃት ግብጽን በመካከለኛ መንግሥት (12ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1832 እስከ 1823 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የአባቱ 3 አመነምሃት ተከታይ ነበር።

4 አመነምሃት
የመዓትኸሩሬ እስፊንክስ ምስል
የመዓትኸሩሬ እስፊንክስ ምስል
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት1832-1823 ዓክልበ.
ቀዳሚ3 አመነምሃት
ተከታይሶበክነፈሩ
ሥርወ-መንግሥት12ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት3 አመነምሃት

በኒመዓትሬ 3 አመናምሃት ዘመነ መንግሥት መጨረሻ ዓመት ልጁን ፬ አመነምሃት ከእርሱ ጋር በጋርዮሽ ወደ ዙፋኑ አስነሣው።

የ፫ አመነምሃትና የልጁ ፬ አመነምሃት ሐውልቶች

የቶሪኖ ቀኖና በተባለው ፈርዖኖች ዝርዝር መሠረት መዓኸሩሬ ለ፱ ዓመታት፣ ፫ ወርና ፳፯ ቀን ነገሠ። በእርሱ ዘመን የማዕድን ጉዞ ወደ ሲና ልሳነ ምድር ከመላኩ በቀር ብዙ ድርጊት አልተፈጸመም። ምንም ልጅ እንዳልነበረው ይመስላል፤ ተከታዩ ሴት ፈርዖን ሶበክነፈሩ ስትሆን ይቺ እኅቱ እንደ ነበረች ይታመናል።

ቀዳሚው
3 አመነምሃት
ግብፅ ፈርዖን
1832-1823 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሶበክነፈሩ