ጸደይ በአማርኛው በልግ፣ የበጋን ወራት ተከትሎ መጋቢት ፳፮ ቀን ይብትና እስከ ሰኔ ፳፭ ቀን ድረስ ከቀላል ዝናብ ጋር ይዘልቃል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ወይም በኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ (የዘመን አቆጣጠር) መሠረት አንድ ዓመት በአራት ንዑሳን ክፍሎች ይከፈላል። ከነኚህ አንዱ ክፍል ወርኀ ጸደይ ነው።


ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ጸደይ የሚለውን ቃል ሲያብራሩ «ዐጨዳ፤ ያጨዳ ወራት፤ ዘመነ በልግ፤ በወዲያ መከር፣ በወዲህ በልግ የሚደርስበት የሚታጨድበት፣ ወዲያውም የሚዘራበት ወርኀ ዘርዕ። ክፍለ ዓመት፤ ያመት ርቦ ፺፩ ቀን ወይም ፫ ወር በሐጋይና በክረምት መካከል ያለ ክፍል።[1]

የወቅት ስምየመግቢያው ቀንየማለቂያው ቀን
መፀው (አበባ/መኸር)መስከረም ፳፮ታኅሣሥ ፳፭
በጋታኅሣሥ ፳፮መጋቢት ፳፭
ፀደይ (በልግ)መጋቢት ፳፮ሰኔ ፳፭
ክረምትሰኔ ፳፮መስከረም ፳፭

ማጣቀሻዎች

  1. ^ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤"መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ።" (፲፱፻፵፰ ዓ/ም); ገጽ ፯፻፵፬ [1]

ምንጭ