ይስማዕከ ወርቁ
ይስማዕከ ወርቁ ኢትዮጵያዊ ወጣት ደራሲ ሲሆን ዴርቶጋዳ በተባለዉ መፅሀፉ በአንባቢዎቹ ዘንድ ታዋቂነትን አግኝቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ዴርቶጋዳ በአንድ አመት ብቻ 10 ጊዜ በመታተም እና በመጀመሪያ እትሙ ከ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በላይ ኮፒዎች በመሸጥ በኢትዮጵያ የመፅሀፍ ሽያጭ ታሪክ የመጀመሪያው መፅሀፍ ነው። ይስማዕከ እስካሁን አስራ አምስት መፅሀፍትን ለህትመት አብቅቷል (የመጀመርያ መፅሀፉ)፣ የወንድ ምጥ የተሰኜው የግጥም መድብል ነው። የቀንድ አውጣ ኑሮ፣ ዴርቶጋዳ፣ ራማቶሓራ፣ ዣንቶዣራ ፣ ዮራቶራድ፣ ዮቶድ፣ ሜሎስ ፣ ተልሚድ ፣ ክቡር ድንጋይ፣ የኦጋዴን ድመቶች፣ ደህንነቱ፣ ተከርቼም እና ዛምራ የተሰኘ ልቦለድ ያበረከተልን ሲሆን የመጨረሻ ስራው ደግሞ በ አምሓራ ክልል ንፁሀን ህዝብ እና ሀገሪቱን እመራታለሁ በሚለው መንግስት መካከል ባለው አለመግባባት እንዲሁም በትግራይ ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ መካከል የሚሞቱትን ሰዎች በግልፅ ቋንቋ "ግፉዓን"በሚል ኢ-ልቦለድ ድርሰት አቅርቦልናል። ከ መጋቢት 2010 ዓ.ም ወዲህ በሀገሪቱ ላይ እየታየ ያለው ኢ-ፍትሐዊነትና የተበላሸ የመንግስት አስተዳደር የብዙ ንፁሀንን ህይወት እያሳጣን መሆኑን ይስማዕከ በ "ግፉዓን" ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል።
References:
- ^ www.facebook.com/Axafos
- ^ "Archive copy". Archived from the original on 2013-07-21. በ2012-08-19 የተወሰደ.
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽጥምቀትልዩ:Searchኢትዮጵያፋሲል ግቢዓፄ ቴዎድሮስውክፔዲያ ውይይት:ምንጭጌሥርዓተ ነጥቦችSpecial:Searchአማርኛአበበ ቢቂላስዕል:Grammar of the Amharic language.pdfፋሲለደስአርሰናል የእግር ኳስ ክለብአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስማንችስተር ዩናይትድኤችአይቪቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴጎንደር ከተማእስልምናሥነ-ፍጥረትክርስትናየኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎችላሊበላየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግኃይሌ ገብረ ሥላሴየኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማመጽሐፍ ቅዱስአባታችን ሆይአቡነ ተክለ ሃይማኖትየቃል ክፍሎችግብረ ስጋ ግንኙነትኢየሱስእምስፋይዳ መታወቂያየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርመንፈስ ቅዱስአዲስ አበባየዋና ከተማዎች ዝርዝር