የብርሃን ዋለታ
የብርሃን ሞገድ ልከ አንድን ገመደ ወደላይ ወደታች ስናደርግ እንደምናገኘው ሞገድ ነው። ማለት የሞገዱ ጉዞ ወደፊት ሲሆን ሞገዱ የሚርገበገበው ወደ ላይ-ወደ ታች ነው። ስለሆነም ሞገዱ ወደፊት ሚጓዝ ቢሆንም የሚርገገበው ግን አቅጣጫ ሊቀይር ይችላል፡ ለምሳሌ ወደ ጎንና ወደ ጎን ሊርገበገብ ይችላል። ይህ የብርሃን ባህርይ መዋለታ ይባላል። ጉዳዩን በገሃዱ አለም ማየት ይቻላል። ብዙ የጸሐይ መነጽሮች የሚሰሩት ብርሃንን ከሚያወለታ ንጥር ነገሮች ነው። ስለሆነም የመነጽሮቹ መስታወቶች የሚያሳልፉት ከነርሱ መዋለታ ጋር የሚስማማውን ክፍል ብቻ ነው። ስለዚህ ሁለት የጸሓይ መነጽሮችን በተለያየ ማዕዘን በማስቀመጥ ከአንዱ ያለፈውን የዋለታ ብርሃን በሌላው መነጽር እንደገና በማጥራት የተለያየ የብርሃን መጠን እንዲያልፍ ማድረግ ይቻላል። ብርግጥ ሁለቱ መነጽሮች በተቃራኒ ማዕዘን የመዋለቱ ከሆነ ከከፍተኛ ብርሃን እስከ ሙሉ በሙሉ ጨለማ እንዲያስተላልፉ ማድረግ ይቻላል።
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchሥርዓተ ነጥቦችጂፕሲዎችዓፄ ቴዎድሮስየአድዋ ጦርነትኢትዮጵያላሊበላአበበ ቢቂላኤችአይቪአማርኛቅዱስ ያሬድዳግማዊ ምኒልክየአክሱም ሐውልትጀጎል ግንብአክሱም2ኛው ዓለማዊ ጦርነትአፈወርቅ ተክሌእርዳታ:ይዞታጥላሁን ገሠሠዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችፋሲል ግቢየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግየቅርጫት ኳስአርሰናል የእግር ኳስ ክለብተስፋዬ ሳህሉአስቴር አወቀየጋብቻ ሥነ-ስርዓትግዕዝሥነ ምግባርቅዱስ ጊዮርጊስ (ሰማዕት)ምሥራቅ አፍሪካየጢያ ትክል ድንጋይእምስመዝገበ ቃላትአዲስ አበባጥሩነሽ ዲባባ