የሐዋርያት ሥራ ፩

ቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው


የሐዋርያት ሥራ ፩ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲሆን የሚያተኩረው በጌታችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርገትና እስከ ጰራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) መምጣት በፊት ሐዋርያት የሠሩት መንፈሳዊ ተግባራት ናቸው ። የጻፈውም ቅዱስ ሉቃስ እንደሆነ በማስረጃ ሙሉበሙሉ ቤተክርስቲያን የምታምነው ነው ይህም በ፳፮ ንዑስ ክፍሎች ይካተታል ።

የሐዋርያት ሥራ ፩
የዋርያት ሥራ ፲፭ ፳፪ ፳፬ በኮዴክ ላውዲያነስ (Codex Laudianus) በ፭፻፶ ዓ ም የተጻፈ
የዋርያት ሥራ ፲፭ ፳፪ ፳፬ በኮዴክ ላውዲያነስ (Codex Laudianus) በ፭፻፶ ዓ ም የተጻፈ
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ቅዱስ ሉቃስ
የመጽሐፍ ዐርስት የሐዋርያት ሥራ
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፭ኛው መጽሐፍ
መደብ የቤተክርስቲያን ታሪክ
የጌታችን መድኃኒታች ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት


ኢየሩሳሌም
የቅዱስ እንድሪያስ ቤተክርስቲያን
ኢየሩሳሌም
የሐዋርያት ሥራ ፩ is located in
ቤተልሔም
ቢታኒያ
ደበረ ዘይት
ቅዱስ ሉቃስ የሐዋርያትን ሥራ የጻፈባት ቅድስት ከተማ ኢየሩሳሌም አካባቢዋ ።


የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፩

ቁጥር ፩ - ፲ ለማስተካከል

1-2፤ቴዎፍሎስ፡ሆይ፥ኢየሱስ፡የመረጣቸውን፡ሐዋርያትን፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ካዘዛቸው፡በዃላ፡እስከዐረገበት፡ቀን፡ድረስ፥ያደርገውና፡ያስተምረው፡ዘንድ፡ስለዠመረው፡ዅሉ፡መዠመሪያውን፡ነገር፡ጻፍኹ፤3፤ደግሞ፡አርባ፡ቀን፡እየታያቸው፡ስለእግዚአብሔርም፡መንግሥት፡ነገር፡እየነገራቸው፥በብዙ፡ማስረጃ፡ከሕማማቱ፡በዃላ፡ሕያው፡ኾኖ፡ለእነርሱ፡ራሱን፡አሳያቸው።4፤ከነርሱም፡ጋራ፡ዐብሮ፡ሳለ፡ከኢየሩሳሌም፡እንዳይወጡ፡አዘዛቸው፥ነገር፡ግን፦ከእኔ፡የሰማችኹትን፡አብ፡የሰጠውን፡የተስፋ፡ቃል፡ጠብቁ፤5፤ዮሐንስ፡በውሃ፡አጥምቆ፡ነበርና፥እናንተ፡ግን፡ከጥቂት፡ቀን፡በዃላ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ትጠመቃላችኹ፡አለ።6፤እነርሱም፡በተሰበሰቡ፡ጊዜ፦ጌታ፡ሆይ፥በዚህ፡ወራት፡ለእስራኤል፡መንግሥትን፡ትመልሳለኽን፧ብለው፡ጠየቁት።7፤ርሱም፦አብ፡በገዛ፡ሥልጣኑ፡ያደረገውን፡ወራትንና፡ዘመናትን፡ታውቁ፡ዘንድ፡ለእናንተ፡አልተሰጣችኹም፤8፤ነገር፡ግን፥መንፈስ፡ቅዱስ፡በእናንተ፡ላይ፡በወረደ፡ጊዜ፡ኀይልን፡ትቀበላላችኹ፥በኢየሩሳሌምም፡በይሁዳም፡ዅሉ፡በሰማርያም፡እስከምድር፡ዳርም፡ድረስ፡ምስክሮቼ፡ትኾናላችኹ፡አለ።9፤ይህንም፡ከተናገረ፡በዃላ፡እነርሱ፡እያዩት፡ከፍ፡ከፍ፡አለ፤ደመናም፡ከዐይናቸው፡ሰውራ፡ተቀበለችው።10፤ርሱም፡ሲኼድ፡ወደ፡ሰማይ፡ትኵር፡ብለው፡ሲመለከቱ፡ሳሉ፥እንሆ፥ነጫጭ፡ልብስ፡የለበሱ፡ኹለት፡ሰዎች፡በአጠገባቸው፡ቆሙ፤

ቁጥር ፲፩ - ፳ ለማስተካከል

11፤ደግሞም፦የገሊላ፡ሰዎች፡ሆይ፥ወደ፡ሰማይ፡እየተመለከታችኹ፡ስለ፡ምን፡ቆማችዃል፧ይህ፡ከእናንተ፡ወደ፡ሰማይ፡የወጣው፡ኢየሱስ፡ወደ፡ሰማይ፡ሲኼድ፡እንዳያችኹት፥እንዲሁ፡ይመጣል፡አሏቸው።12፤በዚያን፡ጊዜ፡ደብረ፡ዘይት፡ከሚባለው፡ተራራ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ተመለሱ፥ርሱም፡ከኢየሩሳሌም፡የሰንበት፡መንገድ፡ያኽል፡የራቀ፡ነው።13፤በገቡም፡ጊዜ፡ወደሚኖሩበት፡ሰገነት፡ወጡ፥ጴጥሮስና፡ዮሐንስም፣ያዕቆብም፣እንድርያስም፣ፊልጶስም፣ቶማስም፣በርተሎሜዎስም፣ማቴዎስም፣የእልፍዮስ፡ልጅ፡ያዕቆብም፣ቀናተኛ፡የሚባለው፡ስምዖንም፣የያዕቆብ፡ልጅ፡ይሁዳም።14፤እነዚህ፡ዅሉ፡ከሴቶችና፡ከኢየሱስ፡እናት፡ከማርያም፡ከወንድሞቹም፡ጋራ፡ባንድ፡ልብ፡ኾነው፡ለጸሎት፡ይተጉ፡ነበር።15፤በዚህም፡ወራት፡ጴጥሮስ፡መቶ፡ኻያ፡በሚያኽል፡በሰዎች፡ማኅበር፡ዐብረው፡በነበሩ፡በወንድሞቹ፡መካከል፡ተነሥቶ፡አለ፦16፤ወንድሞች፡ሆይ፥ኢየሱስን፡ለያዙት፡መሪ፡ስለኾናቸው፡ስለ፡ይሁዳ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡አስቀድሞ፡በዳዊት፡አፍ፡የተናገረው፡የመጽሐፍ፡ቃል፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟፡ነበር፤17፤ከእኛ፡ጋራ፡ተቈጥሮ፡ነበርና፥ለዚህም፡አገልግሎት፡ታድሎ፡ነበርና።18፤ይህም፡ሰው፡በዐመፅ፡ዋጋ፡መሬት፡ገዛ፥በግንባሩም፡ተደፍቶ፡ከመካከሉ፡ተሰነጠቀ፥አንዠቱም፡ዅሉ፡ተዘረገፈ፤19፤በኢየሩሳሌምም፡ለሚኖሩ፡ዅሉ፡ታወቀ፤ስለዚህም፡ያ፡መሬት፡በቋንቋቸው፡አኬልዳማ283፡ተብሎ፡ተጠራ፥ርሱም፡የደም፡መሬት፡ማለት፡ነው።20፤በመዝሙር፡መጽሐፍ፦መኖሪያው፡ምድረ፡በዳ፡ትኹን፥የሚኖርባትም፡አይኑር፤ደግሞም፦ሹመቱን፡ሌላ፡ይውሰዳት፡ተብሎ፡ተጽፏልና።

ቁጥር ፳፩ - ፳፮ ለማስተካከል

21-22፤ስለዚህ፥ከዮሐንስ፡ጥምቀት፡ዠምሮ፥ከእኛ፡ዘንድ፡እስካረገበት፡ቀን፡ድረስ፥ጌታ፡ኢየሱስ፡በእኛ፡መካከል፡በገባበትና፡በወጣበት፡ዘመን፡ዅሉ፥ከእኛ፡ጋራ፡ዐብረው፡ከነበሩት፡ሰዎች፥ከነዚህ፡አንዱ፡ከእኛ፡ጋራ፡የትንሣኤው፡ምስክር፡ይኾን፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ል።23፤ኢዮስጦስም፡የሚሉትን፡በርስያን፡የተባለውን፡ዮሴፍንና፡ማትያስን፡ኹለቱን፡አቆሙ።24-25፤ሲጸልዩም፦የዅሉን፡ልብ፡የምታውቅ፡አንተ፡ጌታ፡ሆይ፥ይሁዳ፡ወደገዛ፡ራሱ፡ስፍራ፡ይኼድ፡ዘንድ፡በተዋት፡በዚች፡አገልግሎትና፡ሐዋርያነት፡ስፍራን፡እንዲቀበል፡የመረጥኸውን፡ከነዚህ፡ከኹለቱ፡አንዱን፡ሹመው፡አሉ።26፤ዕጣም፡ተጣጣሉላቸው፥ዕጣውም፡ለማትያስ፡ወደቀና፡ከዐሥራ፡አንዱ፡ሐዋርያት፡ጋራ፡ተቈጠረ።