ወደ ሮማውያን ፭


ወደ ሮማውያን በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶፮ - ፶፰ ዓ.ም. የጻፈው መልዕክት ነው ። ይህ ምዕራፍ ፭ ሲሆን በ፳፩ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ።

ወደ ሮማውያን ፭
በ፶፮ ፶፰ ዓ.ም. ወደ ሮማውያን ፓፒረስ ፵ ወረቀት ላይ የተጻፈ መልዕክት ። ይህም የሚያሳየው ስብርባሪውን ነው
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ጳውሎስ
የመጽሐፍ ዐርስት ወደ ሮማውያን
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፮ኛው መጽሐፍ
መደብ የጳውሎስ መልዕክት

ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን መልዕክቱን የጻፈበት ምክኒያት አይሁዳውያንና ሮማውያን በሰላም አንድላይ በሮም ለብዙ ዘመን ሲኖሩ ቆይተው ክርስትና በተመሠረተበት ወቅት ፣ አይሁዳውያን ክርስቶስ እኛን ነው የመረጠን ለመንግሥቱ እናንተን አይደለም... ሲሊ ሮማውያን ደግሞ እናንተ ሰቀላችሁት እንጂ ምን አረጋቹህለት... እየተባባሉ እርስበርሳቸው ጥል ስለፈጠሩ እነሱን ለማስታረቅ ጻፈው ።

ቁጥር ፰ስለእውነተኛ ፍቅር ለማስተካከል

እግዚአብሔር ለሰው ያለውን እውነተኛ ፍቅር ያሳያል ።

8፤ነገር፡ግን፥ገና፡ኀጢአተኛዎች፡ሳለን፡ክርስቶስ፡ስለ፡እኛ፡ሞቷልና፥እግዚአብሔር፡ለእኛ፡ያለውን፡የራሱን፡ፍቅር፡ያስረዳል።

ቁጥር ፲፬ሁለተኛ አዳም ለማስተካከል

የክርስቶስ ፪ኛ አዳምነቱን ያሳውቃል እንዲህ ብሎ፣14፤ነገር፡ግን፥በአዳም፡መተላለፍ፡ምሳሌ፡ኀጢአትን፡ባልሠሩት፡ላይ፡እንኳ፥ከአዳም፡ዠምሮ፡እስከ፡ሙሴ፡ድረስ፡ሞት፡ነገሠ፤አዳም፡ይመጣ፡ዘንድ፡ላለው፡ለርሱ፡አምሳሉ፡ነውና።

ቁጥር ፲፱መዳን በክርስቶስ ለማስተካከል

19፤በአንዱ፡ሰው፡አለመታዘዝ፡ብዙዎች፡ኀጢአተኛዎች፡እንደ፡ኾኑ፥እንዲሁ፡ደግሞ፡በአንዱ፡መታዘዝ፡ብዙዎች፡ጻድቃን፡ይኾናሉ።


የጳውሎስ፡መልእክት ወደ ሮማውያንምዕራፍ ፭

ቁጥር ፩ - ፲ ለማስተካከል

1፤እንግዲህ፡በእምነት፡ከጸደቅን፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡በጌታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ሰላምን፡እንያዝ፤2፤በርሱም፡ደግሞ፡ወደቆምንበት፡ወደዚህ፡ጸጋ፡በእምነት፡መግባትን፡አግኝተናል፤በእግዚአብሔር፡ክብርም፡ተስፋ፡እንመካለን።3-4፤ይህም፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥መከራ፡ትዕግሥትን፡እንዲያደርግ፥ትዕግሥትም፡ፈተናን፡ፈተናም፡ተስፋን፡እንዲያደርግ፡እያወቅን፥በመከራችን፡ደግሞ፡እንመካለን፤5፤በተሰጠንም፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡የእግዚአብሔር፡ፍቅር፡በልባችን፡ስለ፡ፈሰሰ፥ተስፋ፡አያሳፍርም።6፤ገና፡ደካማዎች፡ሳለን፡ክርስቶስ፡ዘመኑ፡ሲደርስ፡ስለ፡ኀጢአተኛዎች፡ሞቷልና።7፤ስለ፡ጻድቅ፡የሚሞት፡በጭንቅ፡ይገኛልና፤ስለ፡ቸር፡ሰው፡ግን፡ሊሞት፡እንኳ፡የሚደፍር፡ምናልባት፡ይገኝ፡ይኾናል።8፤ነገር፡ግን፥ገና፡ኀጢአተኛዎች፡ሳለን፡ክርስቶስ፡ስለ፡እኛ፡ሞቷልና፥እግዚአብሔር፡ለእኛ፡ያለውን፡የራሱን፡ፍቅር፡ያስረዳል።9፤ይልቁንስ፡እንግዲህ፡አኹን፡በደሙ፡ከጸደቅን፡በርሱ፡ከቍጣው፡እንድናለን።10፤ጠላቶች፡ሳለን፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡በልጁ፡ሞት፡ከታረቅን፥ይልቁንም፡ከታረቅን፡በዃላ፡በሕይወቱ፡እንድናለን፤

ቁጥር ፲፩ - ፳፩ ለማስተካከል

11፤ይህም፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥አኹን፡መታረቁን፡ባገኘንበት፡በጌታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡በኩል፡በእግዚአብሔር፡ደግሞ፡እንመካለን።12፤ስለዚህ፡ምክንያት፥ኀጢአት፡ባንድ፡ሰው፡ወደ፡ዓለም፡ገባ፥በኀጢአትም፡ሞት፤እንደዚሁም፡ዅሉ፡ኀጢአትን፡ስላደረጉ፡ሞት፡ለሰው፡ዅሉ፡ደረሰ፤13፤ሕግ፡እስከ፡መጣ፡ድረስ፡ኀጢአት፡በዓለም፡ነበረና፥ነገር፡ግን፥ሕግ፡በሌለበት፡ጊዜ፡ኀጢአት፡አይቈጠርም፤14፤ነገር፡ግን፥በአዳም፡መተላለፍ፡ምሳሌ፡ኀጢአትን፡ባልሠሩት፡ላይ፡እንኳ፥ከአዳም፡ዠምሮ፡እስከ፡ሙሴ፡ድረስ፡ሞት፡ነገሠ፤አዳም፡ይመጣ፡ዘንድ፡ላለው፡ለርሱ፡አምሳሉ፡ነውና።15፤ነገር፡ግን፥ስጦታው፡እንደ፡በደሉ፡መጠን፡እንደዚያው፡አይደለም፤ባንድ፡ሰው፡በደል፡ብዙዎቹ፡ሞተዋልና፥ነገር፡ግን፥የእግዚአብሔር፡ጸጋና፡ባንድ፡ሰው፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋ፡የኾነው፡ስጦታ፡ከዚያ፡ይልቅ፡ለብዙዎች፡በዛ።16፤አንድ፡ሰውም፡ኀጢአትን፡በማድረጉ፡እንደኾነው፡መጠን፡እንደዚያው፡ስጦታው፡አይደለም፤ፍርድ፡ካንድ፡ሰው፡ለኵነኔ፡መጥቷልና፥ስጦታው፡ግን፡በብዙ፡በደል፡ለማጽደቅ፡መጣ።17፤በአንዱም፡በደል፡ሞት፡በአንዱ፡በኩል፡ከነገሠ፥ይልቁን፡የጸጋን፡ብዛትና፡የጽድቅን፡ስጦታ፡ብዛት፡የሚቀበሉ፡በአንዱ፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡በኩል፡በሕይወት፡ይነግሣሉ።18፤እንግዲህ፡ባንድ፡በደል፡ምክንያት፡ፍርድ፡ለኵነኔ፡ወደ፡ሰው፡ዅሉ፡እንደ፡መጣ፥እንዲሁም፡ባንድ፡ጽድቅ፡ምክንያት፡ስጦታው፡ሕይወትን፡ለማጽደቅ፡ወደ፡ሰው፡ዅሉ፡መጣ።19፤በአንዱ፡ሰው፡አለመታዘዝ፡ብዙዎች፡ኀጢአተኛዎች፡እንደ፡ኾኑ፥እንዲሁ፡ደግሞ፡በአንዱ፡መታዘዝ፡ብዙዎች፡ጻድቃን፡ይኾናሉ።20-21፤በደልም፡እንዲበዛ፡ሕግ፡ጭምር፡ገባ፤ዳሩ፡ግን፡ኀጢአት፡በበዛበት፥ኀጢአት፡በሞት፡እንደ፡ነገሠ፥እንዲሁ፡ደግሞ፡ጸጋ፡ከጌታችን፡ከኢየሱስ፡ክርስቶስ፡የተነሣ፡በጽድቅ፡ምክንያት፡ለዘለዓለም፡ሕይወት፡ይነግሥ፡ዘንድ፥ጸጋ፡ከመጠን፡ይልቅ፡በለጠ።