ከንቲባ ገብሩ
ከንቲባ ገብሩ (1845 - 1949) እውነተኛ ስማቸው ጎባው ደስታ ሲሆን የአቶ ደስታ ወልደ እስይ እና ወይዘሮ ትርንጎ ተክሌ ልጅ ነበሩ። የተወለዱትም ጎንደር ውስጥ አለፋ ጣቁሳ የሚባል ቦታ ሲሆን፣ ወላጆቻቸው መሳፍንቶች ስላልነበሩ ብዙ እንግልት ደርሶባቸው ካደጉ በሁዋላ በሚስዮን ወደ ውጭ ሄደው ተምረው ሲመለሱ ባሳዩት ችሎታ በራስ መኮንን የሐረር ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ። ቀጥሎም ከአድዋ ጦርነት በሁዋላ በዓፄ ምኒልክ የመጀመሪያው የጎንደር ከተማ ከንቲባ ሆኑ። በዓፄ ዮሐንስ ዘመን በተካሄደው ጦርነት በሱዳኑ መሪ የታሰሩትን እስረኞች እንዲያስለቅቁ ተልከው የተደራደሩት እሳቸው ነበሩ። የእስረኞቹ መለቀቅ ያናደዳቸው እንግሊዞች ግን ሴራ ፈጥረው ዓፄ ምኒልክ እንዲይስርዋቸው አድርገዋል። ከእስር የተለቀቁትም ንግስት ቭክቶሪያ ስትሞት ነበር። በ1930 የመጀመሪያ ፓርላማ ምክትል ፕሬዘደንት ሆኑ። ጣሊያኖች ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያ ፓርላማ ፕሬዘደንት ሆኑ።
ገብሩ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ጀርመንኛ፣ ፈረንሳይኛና እንግሊዝኛ ይናገሩ ነበር። [1]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
ማጣቀሻወች ለማስተካከል
- ^ http://www.dacb.org/stories/ethiopia/gebru_desta.html"Stars Archived ጁላይ 2, 2015 at the Wayback Machine that glitter
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchሥርዓተ ነጥቦችጂፕሲዎችዓፄ ቴዎድሮስየአድዋ ጦርነትኢትዮጵያላሊበላአበበ ቢቂላኤችአይቪአማርኛቅዱስ ያሬድዳግማዊ ምኒልክየአክሱም ሐውልትጀጎል ግንብአክሱም2ኛው ዓለማዊ ጦርነትአፈወርቅ ተክሌእርዳታ:ይዞታጥላሁን ገሠሠዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችፋሲል ግቢየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግየቅርጫት ኳስአርሰናል የእግር ኳስ ክለብተስፋዬ ሳህሉአስቴር አወቀየጋብቻ ሥነ-ስርዓትግዕዝሥነ ምግባርቅዱስ ጊዮርጊስ (ሰማዕት)ምሥራቅ አፍሪካየጢያ ትክል ድንጋይእምስመዝገበ ቃላትአዲስ አበባጥሩነሽ ዲባባ