ኤልቭስ ፕሬስሊ

ኤልቭስ ፕሬስሊ (እንግሊዝኛ፦ Elvis Aaron Presley) አሜሪካዊ ዘፋኝ፣ ሙዚቀኛ እና ተዋናይ ነበር። ጃንዩዌሪ 8 ቀን 1935 እ.ኤ.አ. ተወልዶ በኦገስት 16 ቀን 1977 እ.ኤ.አ. ሞተ።

Elvis Presley promoting Jailhouse Rock.jpg

ስለአንጋፋነቱ ኤልቭስ ለወዳዶቹ «የሮክ ኤንድ ሮል ንጉሥ» በመባል ታውቋል። ከዚህም በላይ ወደ ተዋናይነትና የባሕል ምሳሌ ወደ መሆን ገብቶ ነበር። በፌብሩዋሪ 1 ቀን 1976 እ.ኤ.አ. እኩለ ሌሊት ኤልቭስና ጓደኞቹ በኤልቭስ የግል አውሮፕላን ገብተው ከቴነሲ እስከ ኮሎራዶ ድረስ በርረው «የቂል ወርቅ ዳቦ» ገዝተው በልተው ተመለሱ። ይህም «የቂል ወርቅ ዳቦ». አሰራር ኦቾሎኒ-ቅቤ ፣ የወይን መርማላታ እና የአሳማ ሥጋ ጥብስ አንድላይ ተቀላቅሎ በዳቦ ውስጥ ተበስሎ ነው። ይህ ድርጊት ዝነኛ ሆነለት። እንዲሁም ኤልቭስ የኦቾሎኒ በሙዝ ሳንድዊች ወይንም የኦቾሎኒና ሙዝ በአሣማ ጥብስ ሳንድዊች በጣም እንደ ወደደ ዝነኛ ነው።