አንድማ ግዙ

(64)አለቃ ገብረሀና መሸት ሲል ጠላ ቤት ተቀምጠው ሲጠጡ ቆዩና ሽንት ለመክፈል በጓሮው በኩል ወጣ ብለው በሚሸኑበት ጊዜ ፈሳቸው ያመልጣቸውና ጡጥ ያደርጋሉ። ሰው ሰምቶ ይሆን ብለው ትንሽ ዞር ብለው ሲመለከቱ ኮማሪትዋም ትንሽ ራቅ ብላ እቃ እየፈለገች ኖራ ሰምታ ይሆናል ብለው በመስጋት አህያ እንደሚያባርሩ በመምሰል «ዙር !! ዙር !!» ብለው ሲጣሩ ሴትዮዋ ሰምታ «ኧረ! እኛ አህያ የለንም» ስትል አለቃ መልስ አይጠፋቸውም አይደል «አንድማ ግዙ» አሉ ይባላል።