በጋ ፀሐይ የሚበረታበት፣ ደረቅና ሐሩር የሐጋይ ወራት ተብሎ ይታወቃል። በኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ (ቁጥር ያለው ዘመን) መሠረት ከክረምት በኋላ መስከረም ፳፮ ቀን የሚጀምረው የመፀው (አበባ) ወቅት፣ ጊዜውን ታኅሣሥ ፳፭ ቀን ፈጽሞ ለበጋ ያቀብላል። በጋ የሚያበቃው መጋቢት ፳፭ ቀን ሲሆን ተረካቢው ወቅት ደግሞ ፀደይ (በልግ) ይሆናል።

የወቅት ስምየመግቢያው ቀንየማለቂያው ቀን
መፀው (አበባ)መስከረም ፳፮ታኅሣሥ ፳፭
በጋታኅሣሥ ፳፮መጋቢት ፳፭
ፀደይ (በልግ)መጋቢት ፳፮ሰኔ ፳፭
ክረምትሰኔ ፳፮መስከረም ፳፭