ቅዱስ ላሊበላ በ 1101 አ.ም ታህሳስ 29 ቀን ከ እናቱ ከኬርዮርና ከአባቱ ዛንስዮም ላሰታ ቡግና ወረዳ ሮሃ ከተባለች ቦታ ከ ፍልፍል ቤተ መቅደስ ውስጥ ተወለደ በዚህ ፍልፍል ቤተ-መቅደስ ውስጥ እድገቱን አደረገ ስድስት አመት ሲሞላው ቤተ-መንግስት አባ ዳንእል የተባሉ መምህር ተቀጥረውለት ከ ፊደል እስከ ዳዊት አጠናቆ ከዚያም የተማረውን የፅሁፍ ጥበብ በቤተ ጎሎጎታ ደብረ ሲና በሚገኘው ከ ኪዳነ ምህረት መንበር ታቦት ዙሪያ ላይ እራሱ የተዓፋቸው የሚዐለይበት ዕሁፎቸች ይገኛሉ፡፡


[1]ቅዱስ ላሊበላ 12 አመት ሲሞላው አባቱ ዘንሳዮም 40 አመት ነግሶ በተወለደ በ 76 አመቱ ከዚህ አለም በ ሞት ተለየ ወድያው ብዙም ሳይቖይ እናቱ ኬርዮርና በሞት ተለየች፡፡ ቅዱስ ላሊበላ በ እናቱ ና አባቱ ህልፈተ ህይወተ በደረሰበት ሀዘን የተነሳ ሁሉን ነገር ለመርሳት ና የትምህርት ፍላጎት ለሞሞላት ጉዞውን ወደ ጎጃም በማድረገ አለም ስላሴ ከተባለው ደብር ከመምህር ኬፋ ሃዲሳቱን አጠናቖ በመመረቅ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡[2]


በወቅቱም በኤትዮጵያ ላይ ነግሶ የነበረው ታላቅ ወንድሙ ቅዱሰ ገብረ ማሪያም ነበር ይህ እንዲህ እያለ በ እህቱ ላይ የእሱ ሊነግስ መሆኑ ቅናት አሳደረባት ቅዱስ ላሊበላ ሁሌም እሚጠጣው ባህላዊ መድሃኒት ውስጥ መርዝ በመጨመር ታስቀምጥለታለች አትሙት ያላት ነፍስ ግን የ ሃገሬውን በሃል ምክንያት አድርጎ ሳይቀመስ አይሰጥምና አብሮት የነበረው ዲያቖን የተቀመጠውን መድሃኒት ቀምሶ ወደ ነበረበት ጠረንቤዛ ላይ አንዳሰቀመጠው ወድያውኑ ህይወቱ ታልፋለች ቅዱስ ላሊበላ ይህን ባየ ጊዚ እኔን ለማአፋት የመጣው መድሃኒት የሌላውን ነፍስ አጠፋች በማለት የቀረውን መድሃኒት በመጠጣት ለ ሶሰት ለሊት እንደ ወደቀ ቀረ ከዚያም ነዋሪው ገንዦ ለ መቅበር ሲዘጋጁ የ ሰውነቱ ሙቀት አልተለየውም ነበር ይሄን ጊዜ ወድያው ቅዱስ ላሊበላ ነቃ የተመለከቱት ሰዎች ተደናገጡ ከዚያም ይህ ሁሉ ነገር በ እህቱ መደረጉ ያሳዘነው ቅዱስ ላሊበላ በመነሳት ጉዞውን ወደ ጫካ አደረገ ኑሮውንም ለ ረጅም አመት እዚያው አደረገ ይህ እንዲ እንዳለ ሚስት እምትሆነውን ሴት አገኝ ቤተሰቦን በማስጠየቅ በ ቤተ ክርስትያን ስርአት ተጋብተው ጥቂት አመት እንደቆዩ ጉዞውን እየሩሳሌም አደረገ ለ ተከታታይ 13 አመታትም ቆይታ በሓላ ወደ ባለቤቱ ተመልሶ ከ ውንድሙ ከ ቅዱስ ገብረ ማሪያም ጋር እርቅ በማውረድ ቅዱስ ገብረ ማሪያም ንግስናውን ለ ቅዱስ ላሊበላ በተወለደ በ57 አመቱ በማስረከብ ኑሮውን በ ገዳም አደረገ፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ስልጣን ላይ ከወጣ በሓላ ሕንዓዎችን ለመገንባት አሰበ ከዚያም በጊዜው ከነበሩት አባቶች በተለይ ቀይት ከ ምትባል ባለአባት የጠየቀውን 40 ጊደር ለ መግዛት በ ሚያስችለው ወርቅ ቦታውን ገዝቶ በከርሰ ምድር ውስጥ ያሉትን ሕንዓዎቸ ሊያወጣ ተዘጋጅ፡፡ ቅዱስ ላሊበላ የሚገነባባቸውን መሳሪያዎችለ 10 አመታት አዘጋጅቶ ማለትም በ 1157 አ.ም ነግሶ በ1166 አ.ም ሕንዓውን ገንብቶ ጨረሰ፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ከ 40 አመታት የንግስና ዘመን በሓላ በተወለደ በ 97 አመቱ ሰኔ12 ቀን ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡[3]ቅዱስ ላሊበላ ያስገነባቸው [4]1.ቤተ መድሃኒያለም፤ ቤተማርያም ፡ቤተ መስቀል፡ ቤተ ደናግል እና ቤተ ሚካኤል ፤2.ለየት ብሎ እሚታየው ከላይ እስከ ታች ድረሰስ በመስቀል ቅርዕ የተቀረዐው ቤተ ጊዮርጊስ፤3.ቤተ ገብር፤ልና ቤተ መርቆሪዮስ፤ ቤተ አማኑኤል እና ቤተ ሊባኖስ ይገኛሉ እነዚህንም ታሪክ ለ ሁለት ይከፍላቸዋል ቤተ መድሃኒአለም፤ ቤተ ማሪያም፤ ቤተ መስቀል፤ ቤተ ደናግል፤ ቤተ ሚካኤል፤ ቤተ ጊዮርጊስ በ ምድራዊ እየሩሳሌም በማለት ቤተ ገብርኤል፤ ቤተ መርቆሪስ፤ ቤተ አማኑኤል፤ ቤተ ሊባኖስ በ ሰማያዊ ፤የሩሳሌም ይላቸዋል፡፡

  1. ^ http://www.sacred-destinations.com/ethiopia/lalibela
  2. ^ http://en.wikipedia.org/wiki/Lalibela
  3. ^ http://www.ethiovisit.com/lalibela/39/
  4. ^ http://whc.unesco.org/en/list/18