ስዕል:AmharicTeretinaMisale.pdf

ወደ ገጽ# ለመሄድ
የሚቀጥለው ገጽ →
የሚቀጥለው ገጽ →
የሚቀጥለው ገጽ →

ዋና ፋይል(1,275 × 1,650 pixels, file size: 368 KB, MIME type: application/pdf, 106 pages)

ተረትና፡ምሳሌ

(ከልዩ፡ልዩ፡ምንጮች፡የተቀዳ....



   አበቢላ፥የመስከረም፡ጠላ።   አቡጊዳ፥የተማሪ፡ዕዳ።   አባ፥ልብሱ፡ዳባ፤ውስጡ፡ደባ።   አባያ፡ቢቀና፥ቤት፡ያቀና።   አባይ፡ማደሪያ፡የለው፥ግንድ፡ይዞ፡ይዞራል።   አባይን፡ያላየ፡ምንጭ፡ያመሰግናል።   አባት፡ያበጀው፡ለልጅ፡ይበጀው።   አባት፡ሳለ፡አጊጥ፥ጀንበር፡ሳለ፡ሩጥ።   አገባሻለኹ፡ያለሽ፡ላያገባሽ፥ከባልሽ፡ሆድ፡አትባባሽ።   አጓቱን፡ሲያዩት፥ዐይቡን፡ጨለጡት።   አደባባይ፥አይወድም፡ዐባይ።   አደንጓሬ፥የኽል፡አውሬ።   አህያ፡የለኝም፤ከዥብ፡አልጣላም።   አወን፡ባይ፡ዕዳ፡ከፋይ።   አዘዞ፥አንድም፡ተናዞ፥አንድም፡ሥንቅ፡ይዞ።   አጥብቆ፡ጠያቂ፡እናቱን፡ይረ፟ዳ፟ል።   አያድርስ፡የባል፡ቢስ።   አይበሉት፡እኽል፡ካፈር፡አንድ፡ነው።   አይጠቅም፡ጠላ፥ባልና፡ሚስት፡ያጣላ።   አይጥፍ፡ደብተራ፤ክንፍ፡የለው፡አሞራ።   አለባለቤቱ፡አይነድም፡እሳቱ።   አለዳኛ፡ሙግት፤አለገመድ፡እክት።   አለዋዛው፡ዋዛ፥ቅቤም፡አያወዛ።   አለው፡አለውና፥ሳይመታው፡ቀረ።   አላባት፥ጐመን፡ባጓት።   አላባት፥ዦሮ፡በጡጫ።   አላዋቂ፡ቤት፡እንግዳ፡ናኘበት።   አላዋቂ፡ሳሚ፡ንፍጥ፡ይለቀልቃል።   አላቻ፡ጋብቻ፥ቈይ፡ብቻ፥ቈይ፡ብቻ።   አሞራውም፡በረረ፥ቅሉም፡ተሰበረ።   አንበሳ፡ምን፡ይበላል፧ተበድሮ፤ምን፡ሊከፍል፧ማን፡ተናግሮ።   አንበሳ፡ሲያረጅ፡የዝንብ፡መጫወቻ፡ይኾናል።   አንዱ፡ባንዱ፡ሲሥቅ፥ጀንበር፡ጥልቅ።   አንዱን፡ጥሎ፥አንዱን፡አንጠልጥሎ።   አንድ፡አይነድ፤አንድ፡አይፈርድ።   አንድ፡በሬ፡ስቦ፥አንድ፡ሰው፡አሳቦ።   አንድ፡ያላት፡እንቅልፍ፡የላት።   አንድ፥ከደግ፡ተወለድ፤አንድ፥ከደግ፡ተጠጋ።   አንድ፡ዓመት፡በወዝ፥አንድ፡ዓመት፡በደመ፡ወዝ።   አንጣሪያ፡ላንጣሪያ፡ቢደጋገፍ፥ተያይዞ፡እዘፍ።   አንቃ፡ላንቃ፡ቢደጋገፍ፥ተያይዞ፡እዘፍ።   አንቃ፥ለራሱ፡አይበቃ።   አትኵራ፡ገብስ፥ጐመን፡ባወጣው፡ነፍስ።   እባብ፡ግደል፤ከነበትሩ፡ገደል።   እኽል፡የያዘ፥ፈርዛዛ፤ወርቅ፡የያዘ፡ቀበዝባዛ።   እኽል፡ከበዩ፤ሰው፡ከገዳዩ።   እናት፡ለልጇ፡ጠንቋይ፡ናት።   እንዳየን፡ጤፍ፡አጋየን።   እንስራዋን፡ትታ፥ውሃ፡ወረደች።   አንቱ፡ትተረጕሙ፤አንቱ፡ትደረግሙ።   አንቱም፣አንቱም፡አትዋሹ፥ወደ፡ጓሮ፡ልትሸሹ።   አፍ፡ቢሳሳት፥ዕዳ፤እግር፡ቢሳሳት፡አንጋዳ።   አፍ፡ያለው፡ጤፍ፡ይቈላል።   አፍ፡ሲከዳ፡ከሎሌ፡ይብሳል።   አፍኣው፡ሰንሰለት፥ውስጡ፡ዐውደ፡ነገሥት።   አፍጣኝና፡አቅጣኝ፥እመዳሮ፡እንገናኝ።   አራሪ፡ለማራሪ፤ማራሪ፡ለበራሪ፡ይተው።   አሰድ፥የያዘውን፡አይሰድ።   እባብ፡ግደል፥ከነበትሩ፡ገደል።   እባብ፡ያየ፥በልጥ፡በረየ።   እባብን፥ልቡን፡አይቶ፡እግር፡ነሣው።   እብድ፡የያዘው፡መልክ፡አይበረክትም።   እብድና፡ዘመናይ፡የልቡን፡ይናገራል።   እገድል፡ያለ፡መጋኛ፤እበላ፡ያለ፡ዳኛ።   እግዜር፡ሳይደግስ፡አይጣላም።   እግር፡ይብሳል፤ያበሰብሳል።   እጅግ፡ስለት፡ይቀዳል፡አፎት፤እጅግ፡ብልኀት፡ያደርሳል፡እሞት።   እያየዃት፡የምታሥቀኝ፡ሚስት፡አገባኹ።   እካስ፡ያለ፡ታግሦ፥እጸድቅ፡ያለ፡መንኵሶ።   እኽል፡አላምጦ፤ነገር፡አዳምጦ።   እምዬ፥ጣጣሽ፡በዛዬ።   እናቱ፡ውሃ፡የኼደችበትና፡የሞተችበት፡እኩል፡ያለቅሳሉ።   እኔ፡ዐውቃለኹ፡የቆቅን፡መላ፤ወይ፡በራለች፥ወይ፡ደፍጣለች።   እንግዴህ፡ለርጥ፥አምሮቴ፡ቍርጥ።   እንደ፡እንግዳ፡ደራሽ፤እንደ፡ውሃ፡ፈሳሽ።   እንደ፡የቦ፡ሰልቶ፥እንደ፡ቈንዦ፡ደርቶ።   እንዲያውም፡በመላ፥ፈስ፡ዳልቻ፡ነው።   እንዳገሩ፡ይኖሩ፤እንደ፡ወንዙ፡ይሻ፟ገ፟ሩ።   እንዳያማኽ፡ጥራው፤እንዳይበላ፡ግፋው።   እንዳንድ፡ቃል፡ተናጋሪ፤እንዳንድ፡ሰው፡መስካሪ።   እንዶድን፡በገርነቷ፡ውሃ፡ወሰዳት።   እንጀራን፡ከባዕድ፥መከራን፡ከዘመድ።   እንጃ፥ባፍኽ፡ሙሉ፡ዥብ፡ይንጃጃ።   እንቅልፍ፡ታበዢ፥ከነብር፡ትፋዘዢ።   እንትኑን፡በንትን፡አደረገው፡ብትንትን።   እንትን፡አልንበት፡እንትን፡ገባበት፤እንትን፡አምጪልኝ፥እንትን፡እልበት፤አንቺም፡ነዪ ልኝ፡እንትን፡ትዪልኝ።   እኛ፡ባገራችን፥ዳቦ፡ፍሪዳችን።   እጸድቅ፡ብዬ፡ባዝላት፥ተንጠልጥላ፡ቀረች።   እራትና፡እሳት፥ዐማትና፡ምራት፤ሳይስማሙ፡መሬት።   እርጅና፥ብቻኽን፡ና።   እሰር፡በፍንጅ፤ጣል፡በደጅ።   እሳት፡ቢዳፈን፡የጠፋ፡ይመስላል።   እሳት፡ለፈጀው፡ምን፡ይብጀው፧   እታዘዝክበት፡አውለኻቸው፥ሽፍታ፡በወሰዳቸው።
   በ   በበላኽ፡ገብር፤በሰማኽ፡መስክር።   በባዳ፡ቢቈጡ፤በጨለማ፡ቢያፈጡ።   በገዛ፡ዳቦዬ፡ልብ፡ልቡን፡ዐጣኹት።   በደንባሪ፡በቅሎ፥ቃጭል፡ተጨምሮ።   በድንገት፥አህያ፡ገባ፡እዥብ፡ቤት።   በጠረጠሩ፥ጠጠር፡ይጥሉ።   በጨው፡ደንደስ፥በርበሬ፡ተወደስ።   በኔ፡ሲያዩብኝ፡፥ባንቺ፡ይዩብሽ።   በምድር፡አይቀር፡ብድር።   በዕውር፡ይጠቃቀሱበታል፤በደንቈሮ፡ይሾካሾኩበታል።   በዓል፡ሽሮ፡የከበረ፥ጦም፡ገድፎ፡የወፈረ፡የለም።   በራት፡ዋዛ፥መሳ፡ይመስል።   በቅሎ፥አባትኽ፡ማን፡ነው፡ቢሉት፥እናቴ፡ፈረስ፡ነች፡አለ።   በቈማጣ፡ቤት፡አንድ፡ጣት፡ብርቅ፡ነው።   በሬ፡ሆይ፥ሣሩን፡አየኽና፡ገደሉን፡ሳታይ።   በሰው፡ቍስል፡ዕንጨት፡ስደድበት።   ቢተኙ፥ነገር፡ያገኙ፤ቢነሡ፥ነገር፡ይረሱ።   ባይገባቡ፥በደጃፍ፡ይገቡ።   ባለቤት፡ቢያፍር፥እንግዳ፡ይጋብዝ።   ባለቤት፡ካልጮኸ፥ጎረ፡ቤት፡አይረዳም።   ባለጌ፡የጠገበ፡ዕለት፡ይርበው፡አይመስለውም።   ባለጌን፥ካሳደገው፡የገደለው፡ይጸድቃል።   ባላዋቂ፡ቤት፡እንግዳ፡ናኘበት።   ባልንጀራዬ፡ሲበልጠኝ፥ቍንጣን፡ይፍለጠኝ።   ባልነቃ፡ሠንጥቆ፤ባልደመነ፡በርቆ።   ባልና፡ሚስት፥ሎሚ፡ከኹለት።   ባልንጀራዬ፡ሲበልጠኝ፥ቍንጣን፡ይፍለጠኝ።   ባንድ፡አጕራ፡ኹለት፡አውራ።   ባፍ፡ይጠፉ፥በለፈለፉ።   ባቄላ፥የራብ፡ዱላ።   ባሪያ፥አጋዥ፡ብታገኝ፥መጅ፡ደበቀች።   በረት፡ካልፈላ፥አይላላ።   ብርሌ፡ተነቃ፥አይኾንም፡ዕቃ።   ብርቅና፡ድንቅ፥አላንድ፡ቀን፡አይደምቅ። / ጕድና፡ድንቅ፥አላንድ፡ሰሞን፡አይደምቅ።   ቦይ፡ለውሃ፥ጐመን፡ለድኻ።


   ገ   ገበጣ፥ገበጥባጣ፥ከኢየሩሳሌም፡የመጣ።   ገቢኽን፡ሳታውቅ፡ይሉኝ፡አትበል።   ገባርና፡ድግር፥ሲተካከል፡ያምር። / ድግርና፡ገባር፡ሲተካከል፡ያምር።   ገብስ፥የኽል፡ንጉሥ።   ገዳይ፡በበለሱ፤ድኻ፡በንጉሡ።   ገንዘብ፡የተውሶ፥ጠፋ፡ተጨርሶ።   ገንዘብ፡ካለ፥በሰማይ፡መንገድ፡አለ።   ገንፎ፥እፍፍ፡ቢሉኽ፥ሊውጡኽ።   ጌታ፡ያዛል፤ውሃ፡ይነ፟ዛ፟ል።   ጐኑ፡የኔ፤ቀኑ፡ሠኔ።   ጕድና፡ድንቅ፥አላንድ፡ሰሞን፡አይደምቅ።


   ደ   ደግ፡አድራጊ፡አበደረ፤ክፉ፡አድራጊ፡ተገደረ።   ደግ፡ጎረ፡ቤት፡ውሻ፡ያሳድጋል፤ክፉ፡ጎረ፡ቤት፡ግን፡ዶሮ፡ያረባል።   ደብተራ፥የዘኬ፡ጐተራ።   ደግ፡ብሠራ፡የጠሉኝ፤ክፉ፡ባደርግ፡ምን፡ይሉኝ።   ደግ፡ዐማጭን፡መጦር፤ክፉ፡ዐማጭን፡በጦር።   ደጃፍ፡የመለሰው፤ማጀት፡የጐረሰው።   ደፋር፡ወጥ፡ያውቃል።   ደፋርና፡ጭስ፡መውጫ፡አያጣም።   ዳቦ፡ሲያይ፥ልብ፡ልቡን፤ዳገት፡ሲያይ፥ጥግ፡ጥጉን።   ዳገት፡ዕርሙ፤ሜዳ፡ወንድሙ።   ዳኛ፡ሲገኝ፥ተናገር፤ውሃ፡ሲጠራ፥ተሻገር።   ድኻ፡በቤቱ፡ንጉሥ፡ነው።   ድኻ፡ቢናገር፡አያደምቅ፤ቢጨብጥ፡አያጠብቅ።   ድኻ፥ይበላው፡እንጂ፥ይከፍለው፡አያጣም።   ድኻ፡ተበድሎ፥ማሩኝ፡ይላል፡ቶሎ።   ድመትን፡በቈሎ፡መጠርጠር።   ድንቢጥ፡እንዳቅሟ፡በብር፡ትታገማለች።   ድር፡ቢያብር፥አንበሳ፡ያስር።   ዶሮ፥ሲሉ፡ሰምታ፥ሞተች፡እጪስ፡ገብታ።


   ሀ   ሆድ፡ባዶ፡ይጥላል።   ሆድ፡ያባውን፡ብቅል፡ያወጣዋል።   ሆድ፡ሲያውቅ፡ዶሮ፡ማታ።   ሆድ፡ሲያር፡ጥርስ፡ይሥቃል።


   ወ   ወዶ፡ገባ፥ልብሱ፡ዳባ።   ወይ፡ጣጣ፤በዚህም፡አያስወጣ።   ወር፡አይጸድቅ፥አቦን፡አይጠምቅ፡የለም።   ወርቅ፡ላበደረ፡ዐፈር።   ውሃ፡ቢወቅጡ፥እንቦጭ።   ውሻን፡በርግጫ፡ማለት፦ዕንካ፡ሥጋ፥ማለት፡ነው።   ዋና፡ከቤት፤ጠበቃ፡ከዱለት።


   ዘ   ዘማት፡ለባልንጀራው፦እኔ፡የገደልኹት፡ደም፡አልወጣውም፡ቢለው፦ቤት፡ሠሪውን፡ገድለኽ፡ ይኾናል፡አለው፡ይባላል።   ዘሩ፡የጣቴ፤ምድሩ፡ያባቴ።   ዘር፡ከልጓም፡ይጠቅሳል።


   ዠ   ዥብን፡ሊወጉ፡ባህያ፡ይጠጉ።
   ጠ   ጠጅ፡በብርሌ፤ዜማ፡በሃሌ። / ጠጅ፡በብርሌ፤ነገር፡በምሳሌ።   ጠላት፡ይቀባ፟ል፡ጥላት።   ጠንቋይ፡ለራሱ፡አያውቅም።   ጠፍር፡በሊታ፡ብትኼድ፥ልጓም፡በሊታ፡መጣች።   ጣዝማ፡ይሰረስራል፤ዳኛ፡ይመረምራል።   ጣመኝ፤ድገመኝ።   ጥምድ፡እንደ፡በሬ፤ቅንት፡እንደ፡ገበሬ።   ጥፌ፥ለጭፌ።   ጥርስና፡ከንፈር፥ሲደጋገፍ፡ያምር።   ጦጣ፥ባለቤትን፡ታስወጣ።


   የ   የእብድ፡አሞራ፥ሲላ፡ደንገጥሯ።   የበላ፡በለጠ፤የሮጠ፡አመለጠ።   የበላን፡ያብላላዋል፤የለበሰን፡ይበርደዋል።   የበሬ፡ዶሰኛ፥የሴት፡ምላሰኛ፥አታምጣ፡ወደኛ።   የበሬን፡ውለታ፡አህያ፡ወሰደች።   የባል፡ደግነቱ፥ባትናገር፡ሚስቱ።   የደላው፡ሙቅ፡ያኝካል።   የዘሬን፡ብተው፡ያንዘርዝረኝ።   የኅት፡ልጅ፥ባይወልዱትም፡ልጅ።   የኽል፡ክፉ፥ዐጃ፤የሣር፡ክፉ፥ሙጃ፤የነገር፡ክፉ፥እንጃ።   የጅ፡ብልኀት፥ባርነት፤ያፍ፡ብልኀት፥ጌትነት።   የኃጥኡ፡ዳፋ፥ጻድቁን፡አዳፋ።   የጠበኛ፡ፈስ፡ዐይን፡ፋስ።   የካባን፡ራብ፥የዳባን፡ጥጋብ፡የሚያውቅ፡የለም።   የላሜ፡ልጅ፥ያውራዬ፡ውላጅ።   የሌባ፡ዐይነ፡ደረቅ፥መልሶ፡ልብ፡ያደርቅ።   የሌባን፡ጠበቃ፥አደባልቀኽ፡ውቃ።   የልጅ፡ጥፉ፥በስም፡ይደግፉ።   የሚያድግ፡ልጅ፡አይጥላኽ፤የሚሞት፡ሽማግሌ፡አይርገምኽ።   የማይፈወስ፡ድውይ፤የማይመለስ፡ጊጉይ።   የምጣዱ፡ሳለ፥የዕንቅቡ፡ተንጣጣ።   የሞተውን፡አያ፡ይለዋል።   የነገር፡ጣም፡በዦሮ፤የኽል፡ጣም፡በጕረሮ።   የጠገራ፡ላም፥ባደረችበት፡በረት፡እበት፡አይገኝም።   የጠረጠረ፥ቤቱን፡ዐጠረ።   የመዝሙር፡መዠመሪያ፡ሃሌታ፤የዘፈን፡መዠመሪያ፡እስክስታ።   የነገር፡ወጡ፥ማዳመጡ።   የፈሪ፡በትር፥ዐሥር።   የፉክክር፡በር፡ሳይዘጋ፡ዐደረ።   የረዘመውን፡በጦር፥ያጠረውን፡በድግር።   የራሷን፡አበሳ፡በሰው፡አብሳ።   የሰው፡ገንዘብ፡አይጠገብም።   የሰው፡ወርቅ፡አያደምቅ።   የስንዴ፡ዐራራ፥የቈንዦ፡መራራ።   የሹሮ፡ድንፋታ፥እንጀራ፡እስኪመጣ።   የሺ፡ፍልጥ፥ማሰሪያው፡ልጥ።   የተጠማ፡ከፈሳሽ፤የተበደለ፡ከነጋሽ።   የተከፋ፡ተደፋ።   የተናገሩት፡ከሚጠፋ፥የወለዱት፡ይጥፋ።   የታዘለ፡በለምድ፥የተረገዘ፡በሆድ።   የታጠበ፡እጅ፥ያልባለቀ፡ልጅ።   የቸገረው፡ዱቄት፡ከነፋስ፡ይጠጋ።   የት፡ነው፡አገርኽ፧አህያ፡ፈጅ።ከማዞር፡ከመጠምጠም፡እንዲያው፡ዥብ፡ነኝ፡አትልምን፧   የትም፡ፍጪው፥ዱቄቱን፡አምጪው።   የትም፡ተወለድ፤አንኮበር፡እደግ።   ያቡን፣የጨጌ፡ከብት፥በየወገኑ፡ይከተት።   ያባያ፡ልጅ፡ወዳቂ፥ያራኝ፡ልጅ፡አጥባቂ።   ያባት፡ወዳጅ፤የደንጊያ፡ገድጋጅ።   ያህያ፡ባል፡ከዥብ፡አያስጥል።   ያወቀ፥ተጠነቀቀ፤የዘነጋ፥ተወጋ።   ያውሬ፡ሥጋ፥ለወሬ።   ያኵራፊ፡ምሳ፡ራት፡ይኾናል።   ያለኽ፡ምዘዝ፥የሌለኽ፡ፍዘዝ።   ያልገደለ፡ዘማች፤ያልወለደ፡ዐማች።   ያልወለድኹት፡ልጅ፡አባባ፡ቢለኝ፤አፌን፡ዳባ፡ዳባ፡አለኝ።   ያልጠረጠረ፡ተመነጠረ።   ያልተሾመ፡አያዝ፤ያልቀሰሰ፡አይናዝዝ።   ያመኑት፡ፈረስ፥በደንደስ።   ያምራል፡ብሎ፡ከመናገር፥አያምርም፡ብሎ፡መተው።   ያምሯል፤ይታደሏል።   ያፍ፡ዘመድ፥በገበያም፡አይገድ።   ያረገዘች፡ታስታውቅ፥ከደረቷ፡ትታጠቅ።   ያረረበት፡ያማስላል።   ያራኝ፡ልጅ፥አጥባቂ፤ያባያ፡ልጅ፥ወዳቂ።   ያስቡት፡አይገድ።   ያተር፡ክምር፥የጪሰኛ፡ክብር።   ይሉኝታ፥የራስ፡ዐሊን፡ቤት፡የፈታ።   ይሉኝታና፡መጠቀም፡ባንድነት፡አይገኝም።   ይመስል፥አይመስል፤የጠይብ፡እጁ፡ተከሰል።


   ከ   ከበሮ፥በሰው፡እጅ፡ያምር፤ሲይዙት፡ያደናግር።   ከጌታ፡ግልምጫ፥ከዳገት፡ሩጫ፥ከባለጌ፡ጡጫ፥(ሰውረኝ)።   ከዳቦ፡የተገኘ፡ወጥ፥ዐብረኽ፡ግመጥ።   ከገንዘብ፡ርስት፥ከከብት፡እንስት።   ከባለቤት፡ያወቀ፡ቡዳ፡ነው።   ከወገብ፡በታች፡ጣዖት፤ከወገብ፡በላይ፡ታቦት።   ከወገኑ፡የተለየ፡አንበጣ፡ይኾናል፡ፌንጣ።   ከጥላ፡ያረፉ፤ከሞት፡የተረፉ።   ከይሉኝ፡አይል፡ዐይብ፡አትብላ፤አይመረው፥አይተኵሰው፤ውጦ፥ውጦ፡ይጨርሰው።   ከክፉ፡ባለዕዳ፡ጐመን፡ዘር፡ተቀበል።   ከልጅ፡አትጫወት፤ያወጣኻል፡በንጨት።   ከልጅ፡ክፉ፥ዲቃላ፤ከኽል፡ክፉ፥ባቄላ፤ከልብስ፡ክፉ፥ነጠላ።ጠላት፡ይገፋል፡ዲቃላ፤ራብ ፡ይከላል፡ባቄላ፤ቀን፡ያሳልፋል፡ነጠላ።   ከመደብደብ፡ይሻላል፡ማደብ።   ከመጠምጠም፥መማር፡ይቅደም።   ከመልካም፡ጠላ፥ክፉ፡ጠጅ፤ከመልካም፡ጎረ፡ቤት፥ክፉ፡ልጅ።   ከመምሩ፥ደቀ፡መዝሙሩ።   ከመረቁ፡አውጡልኝ፤ከሥጋው፡ጦመኛ፡ነኝ።   ከመቶ፡ዐምሳ፡ዳዊት፥የልብ፡ቅንነት።   ከሜዳ፡ወዲያ፡ፈረስ፥ካርባ፡ወዲያ፡ቄስ።   ከምድር፡አደላድሎ፡ካህያ፤ከቡላድ፡አደላድሎ፡ከቋያ።   ከነገረኛ፡ሰው፡ሥንቅ፡አይደባልቁም።   ከነገሩ፥ጦም፡ዕደሩ።   ከኛ፡ወዲያ፡ጐራሽ፥እኽል፡አበላሽ።   ከናት፡ወዲያ፡ዘመድ፥ከቃጫ፡ወዲያ፡ገመድ።   ከሩቅ፡ዘመድ፥የቅርብ፡ጎረ፡ቤት።   ከሰው፡ክፉ፥ደባል፤ከጭነት፡ክፉ፥አላል።   ከሰው፡ክፉ፥ደብተራ፤ካውሬ፡ክፉ፥ዳሞትራ።   ከሰው፡ቀለብላባ፥ከመሬት፡ገብጋባ።   ከሺ፡ደብተራ፥የቄስ፡ደንካራ።   ከሺ፡ምስክር፡የታቦት፡እግር።   ከተሟጋች፡ታራቂ፤ካጣቢ፡አድራቂ።   ካገር፡ደጋ፤ከመኝታ፡ዐልጋ። / ካገር፡ወይና፡ደጋ፤ከመኝታ፡አልጋ።   ካጕል፡ጥንቈላ፥የሰው፡ልጅ፡መላ።   ካላ፟ህ፡አልኾንኹ፥ከነቢ።   ካልጠገቡ፡አይዘሉ፤ካልዘለሉ፡አይሰበሩ።   ካልሠሩ፡በጣም፥ገንዘብ፡አይመጣም።   ካንዠት፡ካለቀሱ፡እንባ፡አይገድም።   ካፍ፡የወጣ፡አፋፍ፡(ነው)።   ክስ፡በክሱ፤ሥጋን፡በኵበት፡ጠበሱ።


   ኸ   ኹለት፡ጥፉ፥ካገር፡ይጠፉ።   ኹለት፡ቍና፡ሰጥቼ፥አንድ፡ጥንቅል።


   ለ   ለዳኛ፡አመልክት፥እንዲኾን፡መሠረት።   ለወጡ፡ዕዘኑለት፥ከንጀራውም፡ጕረሡለት።   ለወሬ፡የለው፡ፍሬ፤ላበባ፡የለው፡ገለባ።   ለጥምቀት፡ያልኾነ፡ቀሚስ፥ይበጣጠስ።   ለጦም፡ግድፈት፤ለበዓል፡ሽረት።   ለይቶት፡አባ፡ንጉሧ።   ለሙት፡የለው፡መብት።   ለራሱ፡አያውቅ፡ነዳይ፥ቅቤ፡ለመነ፡ላዋይ።   ለሰው፡ብሎ፡ሲያማ፥ለኔ፡ብለኽ፡ስማ።   ለሰው፡ልጅ፡ሲያበሉ፥ለውሻ፡ልጅ፡ያብሉ።   ላገሩ፡እንግዳ፥ለሰዉ፡ባዳ።   ላህያ፡ማር፡አይጥማት።   ላይሞቱ፡መናዘዝ፤ላይመቱ፡መጋበዝ።   ላይን፡አምላክ፡አለው።   ላይንና፡ለወዳጅ፡ጥቂት፡ይበቃዋል።   ላም፡ሲበዘበዝ፥ጭራውን፡ያዝ።   ላምጪ፡ይግደደው።   ላንድ፡ብርቱ፥ኹለት፡መድኀኒቱ።   ላፍ፡ግም፥አፍንጫ፡ድፍን፡ያዝለታል።   ላሳር፡የጣፈው፡ቢነግድ፡አይተርፈው።   ሌባን፡ሌባ፡ቢሰርቀው፥ምን፡ይደንቀው።   ሌሊት፡ላራዊት፥ቀን፡ለሰራዊት።   ልጅ፡ያለልጅ፡አከለ።   ልጅና፡ጦጣ፥ውሃ፡ይጠጣ።   ልፋት፡ቢያምርኽ፥መሬት፡ግዛ፤ችግር፡ቢያምርኽ፥ልጅ፡አብዛ።
   መ   መጓጓት፡ያከሳል።   መሶብ፡ሰፍቼ፥ላጤ፡አበርክቼ።   ማቅ፡ይሞቃል፤ጋቢ፡ይደምቃል፤ገቢውን፡ባለቤት፡ያውቃል።   ሜ፡ባልኩ፥ፍየል፡ከፈልኩ።   ምን፡ብታፈገፍጊ፥ተግድግዳ፡አታልፊም።   ምን፡ያመጣል፡ሠኔ፤ምን፡ይሠራል፡ቦዘኔ።   ምን፡ቢያርሱ፥እንደ፡ጐመን፡አይጐርሡ።   ምን፡ቢነግሡ፥በገዛ፡እጅ፡አይካሱ።   ምንም፡በሙቱ፥ዐራድማ፡ሸምቱ።   ምንም፡ብጠላው፥በወንድሜ፡ግንባር፡ደም፡አልይበት።   ሞኝ፡የያዘው፡ፈሊጥ፥ውሻ፡የያዘው፡ሊጥ።   ሞኝ፡የለቱን፥ብልኽ፡ያመቱን።   ሞት፡ሲደርስ፥ቄስ፤ጦር፡ሲደርስ፡ፈረስ።


   ነ   ነገሩ፡ነገር፡ነው፤ውስጡ፡ጥቅንጥቅ፡ነው።   ነገር፡ቢበዛ፡ባህያ፡አይጫንም።   ነገር፡ባዋቂ፥ብረት፡በጠራቂ።   ነገር፡ከግቡ፤ጋሻ፡ከንግቡ።   ንጉሥ፡ከሠየመው፡ማረሻ፡የሾመው።   ንግርና፡ግግር፥ሳይደርስ፡አይቀር።


   ሠ   ሠላሳ፡ቢታለብ፥እኔ፡በገሌ፡አለች፡ድመት።   ሥጋ፡ቍጠር፡ቢሉት፦ጣፊያ፡አንድ፥አለ።


   ዐ   ዐባይ፡ጠንቋይ፡ቤት፡ያፈርሳል።   ዐብሮ፡ማደግ፡ያናንቃል።   ዐደራ፡ቢሏቸው፥ይብሳሉ፡እሳቸው።   ዐደራ፡ጥብቅ፤ሰማይ፡ሩቅ።   ዐውድማ፡ላመለጥ፤ምስክር፡ላበለጥ።   ዐጤን፡ይበልጡ፡ቀላጤ፥ሙክትን፡ይሻል፡ወጠጤ።   ዐጤን፡መደብ፤ይቴጌን፡ገደብ።   ዐይጥ፡በበላ፥ዳዋ፡ተመታ።   ዐይጥ፡ለሞቷ፡የድመት፡አፍንጫን፡ታሸታለች።   ዐሮ፟ም፡መሮም፥ማበሬን፡ከፈልኹ።   ዐሎ፡ብሎ፡የተረታ፥መኻል፡አገዳውን፡የተመታ።   ዓለም፡ዐላፊ፥መልክ፡ረጋፊ።   ዓሣ፡ያለበት፡ባሕር፥ዕውር፡ያለበት፡ደብር፥ሳይበጠበጥ፡አያድር።   ዕዳ፡በድግጣ።   ዕዳው፡ዶሮ፥መጋቢያው፡ዳወሮ።   ዕድሜ፡ለንስሓ፥ዘመን፡ለፍሥሓ።   ዕድሜና፡ጨርቅ፥እንደ፡ምንም፡ያልቅ።   ዕውቀትና፡ፍጥረት፡አንድ፡ቀን፡ነው።   ዕውር፡ቢወበራ፥ከመሪው፡ይጣላ።   ዕውር፡ያለበት፡ደብር፥ዓሣ፡ያለበት፡ባሕር፥ሳይበጠበጥ፡አያድር።   ዕንጨት፡ኹኖ፡የማይጨስ፥ሰው፡ኹኖ፡የማይበድል፡የለም።


   ፈ   ፈጥኖ፡መስጠት፤ዃላ፡ለመፀፀት።   ፊት፡ወዳጅኽን፡በምን፡ቀበርከው፧በሻሽ፤የዃለኛው፡እንዳይሸሽ።   ፊት፡የደረሰን፡ወፍ፡ይበላው፤ፊት፡የተናገረን፡ሰው፡ይጠላው።   ፌንጣ፡ብትቈጣ፥እግሯን፡ጥላ፡ኼደች።   ፍየል፡ከመድረሷ፥ቅጠል፡መበጠሷ።


   ጸ   ጺም፡የሌለው፡መምር፤ዐጸድ፡የሌለው፡ደብር።
   ቀ   ቀይ፡እንደ፡በርበሬ፤ጠሩ፡እንደ፡ብርሌ።   ቀን፥በበቅሎ፤ማታ፡በቈሎ።   ቀን፡ከጣለው፥ዅሉ፡የጠላው።   ቀን፡ለተባባሰው፥ማጭድ፡አታውሰው።   ቅቤ፡መዛኝ፡ድርቅ፡ያወራል።   ቍንጫ፡የተጠረገ፡ዕለት፥ባለጌ፡የተመከረ፡ዕለት።


   ሰ   ሰባት፡ዓመት፡ባይማሩ፥ሰባ፡ዓመት፡ይደነቍሩ።   ሰዶ፡ማሳደድ፡ቢያምርኽ፥ዶሮኽን፡ለቆቅ፡ለውጥ።   ሰው፡እንግዳ፡ቢኾን፥እግዜር፡ባላገር፡ነው።   ሰው፡ከሞት፡ወዲያ፥ከወረደ፡አንጋዳ፥ወዳጁን፡አይጠቅም፥ጠላቱን፡አይጐዳ።   ሰውን፡ማመን፡ቀብሮ፡ነው።   ሰይጣን፡ጦመኛ፡ሲኾን፥ዘላለም፡ሰይጣን፡ነው።   ሰይጣን፡ለወዳጁ፡ደርብ፡ነው።   ሰነፍ፡እረኛ፡ከሩቅ፡ይመልሳል።   ሲገደገድ፡ያልበጀው፥ሲዋቀር፡እሳት፡ፈጀው።   ሲወጡ፡እንደ፡ጦጣ፤ሲወርዱ፡ዐሳር፡መጣ።   ሲጠባ፡ያደገ፡ጥጃ፥ቢይዙት፡ይጓጕራል።   ሲያረጁ፡አይበጁ።   ሲያረጁ፡አንባር፡ይዋጁ።   ሲታጠቡ፡ከክንድ፥ሲታረቁ፡ከሆድ።   ሳይጠሩት፡ወይ፡ባይ፥ሳይሰጡት፡ተቀባይ።   ሳይጣሉት፡የተጣላ፥ሲርብ፡ያበላ።   ሳይቸግር፡ጤፍ፡ብድር።   ሳትወልድ፡ብላ።   ሴት፡ሲበዛ፥ጐመን፡ጠነዛ።   ሴት፡ታውቅ፤በወንድ፡ያልቅ።   ስለት፡ድጕሱን፥ደባ፡ራሱን።   ስምኽ፡ማን፡ነው፧ላገር፡አይመች።ማን፡አወጣልኽ፧አሮጋግቶች።   ስምኽ፡ማን፡ነው፧ላገር፡አይመች።ማን፡አወጣልኽ፧ጎረባብቶች።   ስምንተኛው፡ሺ፥ሰው፡አበላሺ።


   ሸ   ሸዋ፡ባላመጠ፥ባመቱ፡ይውጣል።   ሹመት፡በተርታ፤ሥጋ፡በገበታ።


   ተ   ተግደርዳሪ፤ጦም፡ዐዳሪ።   ተጠማኝ፡ሲሰነብት፡ባለርስት፡ይኾናል።   ተጥዶ፡የማይፈላ፤ተሹሞ፡የማይበላ።   ተፈጥሮን፡ተመክሮ፡አይመልሰውም።   ተረቴን፡መልስ፥አፌን፡በጨው፡አብስ።   ትልቁ፡ዳቦ፡ሊጥ፡ኾነ።


   ቸ   ቸርን፡ቢያጠብቁት፡ቢስ፡ይኾናል።
   ጰ   ጳጉሜ፡ቢወልስ፥ጐተራኽን፡አብስ።

የፋይሉ ታሪክ

የቀድሞው ዕትም ካለ ቀን/ሰዓቱን በመጫን መመልከት ይቻላል።

ቀን /ሰዓትናሙናክልሉ (በpixel)አቅራቢውማጠቃለያ
ያሁኑኑ23:19, 30 ሜይ 2011በ23:19, 30 ሜይ 2011 የነበረው ዕትም ናሙና1,275 በ1,650፣ 106 ገጾች (368 KB)Hgetnet (ውይይት | አስተዋጽኦ)

የሚከተለው ገጽ ወደዚሁ ፋይል ተያይዟል፦

ተጨማሪ መረጃ