ስልጤ

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ብሄር

የስልጤ በሀገራችን ከሚገኙ በርካታ ብሔሮች: ብሔረሰቦችና ህዝቦችአንዱ ነው: ብሔረሰቡ በአዲስ አበባ-ሆሳዕና መንገድ በ172 ኪ.ሜ ርቀትከመንገዱ ግራና ቀኝ 60 ኪ.ሜ ያህል ገባ ብሎ በሚገኘው በደቡብ ክልልስልጤ ዞን በስፋት ይኖራል የዞኑ ጠቅላላ ስፋት 3ሺkm² ነው:: እኤአ 2004በተደረገ ቆጠራ በዞኑ የሚኖረው 850ሺ በዞኑ መስደደር ቢቻ የነበረ ሲሆን የዞኑተወላጆች ያዞኑ ህዝብ በሁኑ ሰዓት ከ900ሺ በለይ ይሆናል ተቢሎ ይታሰበል።ከዞኑ በተጨማሪ ከ1 ምሊዬን በለይ ከዞኑ ጎራቤት ካጉራጌ፣ካሀድያ ፣ካኣለበ ናካኦሮሞ ቤሔራሰቦች ታቀለቅሎ ሳፍሮወል እነም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎችናየውጪ ሀገራትም በስፋት ተሰራጭተው ይኖራሉ:: ከብሔረሰቡ 45% የሚሆነውየእስልምና ዕምነት ተከታይ ነው::0.9 % የኣመራና የሌላ ብሔርሰብ ኦርቶዶክስክርታን ይኖርበታል ።ከዞኑ ውጭ የሉ ስልጤዎች 100% የስልምና ተካታይ ሲሆኑበታጫር ከ99 % በለይ በከፍል ስልጤ ሙስልሞች ነቸው። መለትም በኣበትዎይም በእነት የስልጤ ዝርየነት የለቸው ነቸው።ግብርና ዋነኛ የኢኮኖሚመሠረት ሲሆን ከብት አርባታና ንግድም እንዲሁ የብሔረሰቡ የሀብት ምንጭናቸው::.. ዞኑ አሁን በስምንት ማለትም:- ምዕራብ አዘርነት:ምስራቅአዘርነት:አልቾውሪሮ:ዳሎቻ:ላንፎሮ:ሳንኩራ :ሁልባረግና ስልጢ ወረዳዎችየተዋቀረ ነው::የብሔረሰቡ ቋንቋ ስልጢኛ ሲሆን ከሴማዊያን ቤተሰቦችይመደባል .. የቋንቋው ስፋት ከሀረሪኛና የዛይ ቋንቋ ጋር በጣም ሲመሳሰልበበርካታ የቃላት ትርጉዋሜ ደረጃ ከአረብኛ: አማርኛ ትግርኛ አርጎቢኛና ኦሮምኛጋርም ይገናኛል::"ስልጤ" የሚለው ስም በዞኑ በሚገኙ በዋነኛነት አምስት ማኅበረሰቦች ማለትምስልጢ:መልጋ:ሁልባረግ:አዘርነት በርበሬና አልቾውሪሮ የጋራ መጠሪያ ሲሆንማኅበረሰቦቹ በታሪክ: በማኅበራዊ ኑሮ :በባህል: በቋንቋና በሀይማኖት እንዲሁተመሳሳይ ናቸው የስያሜውን መነሻ በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎች ያሉ ሲሆንስያሜውን ያገኘው ከሀጂ አሊዬ 5ተኛ ልጅ ከሆኑት ገን-ስልጤ አልያምሱልጣኔት ከሚለው አረብ ኢስላማዊ መንግስት ጥንታዊነት እንዲሁም ነባርኢስላማዊ መንግስታትና ማኅበረሰቦች የታሪክ ወራሽነትን በማሰብ ነው የሚለውበስፋት ይገለፃል::ስልጤ የምጣረበቸው ታጨመር ስሞች `` እስላም``ታብሎ ስጣራ ፡ ቋንቋቸው`እስለምኛ `በመበል በደቡብ ክፍል እስከ ዘሬ ይታዎቀል .ክሰሜን' ጉራጌ` ታብሎየምታዎቅ ብሆንም ስልጤ የረሱን ዞን ከመሰራተ ጀምሮ ስሙ ለይመለስቀርቶዎል።የስልጤ ብሔረሰብብሔረሰቡ በዋናነት በክልሉ በስልጤ ዞን ውስጥ በሚገኙ ስምንት ወረዳዎችበሀገር ውስጥ ፣ በዎላይታ፣ በሲዳማ እና ጌዲኦ ዞኖች፣ በሀዋሣ ከተማ እናበሀላባ ልዩ ወረዳ እንዲሁም ከክልሉ ውጪ በጂማ፣ በወለጋ፣ በናዝሬት /አዳማ/፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በአደስ አበባ ከተሞች ከሌሎች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦችጋር በስብጥር ይኖራሉ፡፡ብሔረሰቡ በዋናነት የሚኖርበት ሥፍራ በሰሜን እና በሰሜን ምዕራብ የጉራጌዞን፣ በደቡብ የሀዲያ ዞን እና የሀላባ ልዩ ወረዳ፣ በምዕራብ የሀዲያ ዞን ፣በምስራቅ የኦሮሚያ ክልል ያዋሰኑታ፡፡የብሔረሰቡ ዋነኛ መገኛ ሥፍራ መልክዐ ምድራዊ አቀማመጥ በአብዛኛውሜዳማ ሲሆን የተወሰነው በተለይም ምዕራባዊው ክፍል ተራራማነት ያለው ነው፡፡የአየር ንብረቱ በተለያዩ ደረጃ ደጋማ፣ ወይናደጋማ እና ቆላማ ሲሆን አብዛኛውክፍል ወይናደጋማ ነው፡፡ የሕዝቡ ኢኮኖሚ የተመሰረተው በዋናነት በእርሻ ሲሆንከዚሁ ጐን ለጐን የተወሰነው ክፍል የከብት እርባታን፣ ንግድን፣ እና አንዳንድ የእደጥበብ ውጤታችን በማምረት ኑሮአቸውን ይመራሉ፡፡ በዋናነት ከሚመረቱ የእርሻምርቶች መካከል በርበሬ ፣እንሰት፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ ፣ ገብስ፣ አተር፣ ባቄላ፣ቦሎቄ፣ አደንጓሬ፣ ቡና፣ ጫት፣ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ቋንቋየስልጤ ብሔረሰብ አፍ መፍቻ ቋንቋ ስልጢኛ ሲሆን ከሴማዊ የቋንቋ ቤተሰብይመደባል፡፡ ቋንቋው ከአረብኛ፣ ከጉራጊኛ ፣ ከሐረሪ፣ ቋንቋዎች ጋር ይመሳሰላል፡፡የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ በከተሞች አካባቢ ያሉአማርኛን እንዲሁም እንደ አጐራባችነታቸውና ቅርበታቸው የሀድይኛ፣ የማረቆኛ፣የጉራግኛ፣ የኦሮምኛ እና የሀላብኛን ቋንቋዎች በሁለተኛ ደረጃ ይናገራሉ፡፡ሌሎችም አጐራባች ብሔረሰቦች እንዲሁ የስልጢኛን ቋንቋ እንደየቅርበታቸውለመግባቢያነት ይጠቀማሉ፡፡ስልጢኛ ከ6ዐ ዓመት በፊት የአረብኛ ፊደልን በመጠቀም ለጽሑፍ የዋለ ቋንቋቢሆንም ከ1967 ዓ/ም ጀምሮ ልዩ ልዩ አዋጆች እና የመሰረተ ትምህርትማስተማሪያ መጽሐፍት የሳባ ፊደልን በመጠቀም በቋንቋው ተተርጉመዋል፡፡ከ1987 ዓ/ም ጀምሮ የ1ኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሣይክል የመማሪያ መጽሐፍትበቋንቋው ተዘጋጅተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የትምህርት ቋንቋ ሆኖ በማገልገል ላይይገኛል፡፡ እንደዚሁም የሣባ ፊደልን በመጠቀም የመማሪያ መጽሐፍት፣ የስልጢኛመዝገበ ቃላት፣ የስልጤ ሕዝብ ታሪክ እና ሌሎች መጽሀፍቶች በቋንቋውተጽፈው አገልግሎት እየሠጡ መሆናቸው ቋንቋው በማደግ ላይ ያለ ስለሚሆኑየሚገልፁ እውነታዎች ናቸው፡፡ታሪካዊ አመጣጥየስልጤን ብሔረሰብ ታሪካዊ አመጣጥ በተመለከተ በብሔረሰቡ የዕድሜባለፀጋዎች የሚነገሩ የትውፊት እና አንዳንድ የተገኙ የጽሑፍ መረጃዎችንበሁለት መልኩ ከፍለን እንመለከታለን፡፡ የመጀመሪያው የትውፊት መረጃእንደሚያመለክተው በጥንት ጊዜ ዛሬ የብሔረሰቡ አባላት በሚኖሩበት ሥፍራ"ዡራ" ወይንም "ሀርላ" በመባል የሚታወቁ ሕዝቦች ይኖሩ እንደነበር ይገልፃል፡፡ሌላው መረጃ ደግሞ በ8ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ የተወሰኑ ቀደምትየብሔረሰቡ አባላት ከምድረ ሣውዲ አረቢያ ተነስተው የኤደን ባህረ ሰላጤንአቋርጠው በስተምስራቅ አቅጣጫ በዘይላ ደሴት በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡያመለክታል፡፡ እነዚህ ሕዝቦች በፀሐይ መውጫ አቅጣጫ ወደ አገሪቱ ክፍልከገቡ በኋላ በሐረር ጀበርቲ ዛሬ “አደሬ” ወይንም "ሐረሪ" በሚባለው አካባቢቆይታ አድርገው ወደ ዛሬው መገኛ ሥፍራ በመምጣት ከነባሩ ሕዝብ ጋርተቀላቅለው መኖር እንደጀመሩ ይነገራል፡፡የነዚህ ክፍሎች አመጣጥ በአብዛኛው እስልምናን ከማስተማር ጋር የተያያዘእንደነበር የተገኙ የትውፊት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የተወሰኑ የብሔረሰቡአባላት ደግሞ የግራኝ መሀመድ ወረራ ካበቃ በ1ዐኛው ዓመት ገደማከ1553/63 በሀጂ አልዬ መሪነት የተለያዩ ቦታ እየሠፈሩ አሁን በዋናነት ወደሚኖሩበት አካባቢ እንደደረሱ ይነገራል፡፡ ሀጂ አልዬ በአባታቸው ኢትዮጵያዊበእናታቸው የአረብ ዝርያ እንዳላቸው የሚነገር ሲሆን በስፍራው ሲደርሱበመጀመሪያ መቀመጫቸውን ያደረጉት አልቾ ወሬሮ ላይ እንደነበር በታሪክይነገራል፡፡ በዚያን ወቅት የነበረው የስልጤ ሕዝብ ወደአሁኑ ስፍራ ከመድረሱበፊት ገደብ ዝዋይ / ላቂ ደንበል/፣ ሲዳማ፣ አሊቶ ዳገት /ቡልቡላ አጠገብ/በሚባሉ አካባቢዎች ቆይታ እንዳደረገ የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በወቅቱለሕዝቡ እንቅስቃሴ እንደምክንያት የሚገለፀው በግራኝ መሀመድ የተነሣ ጥሩየመኖሪያ አካባቢ ለመፈለግ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በታሪክ አጥኚዎች ደሞ እንደሚነገረው ስልጤ ጙራጌ እና ሌሎች በአካባቢው የሚገኙ ብሄረሰቦች፥ በቋንቋቸው፡ በደማቸው ጥናት (ጀነቲክስ)፡ በስነ ልቦናቸው፥ በባህላቸው ወዘተ፥ ከሰሜን ኢትዮጵያ በተለይ ከዐማራ ብሄር በ8ኛው-10ኛው ክፍለ ዘመን ፈልሰው በአካባቢው የሰፈሩ ሰፋሪዎች እንደሆኑ ያመላክታል። ይህም ጊዜ ከኦሮሞ ፍልሰት 5መቶ-7መቶ አመታት በፊት ነው።