ስልጢኛኢትዮጵያ የሚነገር ቋንቋ ሲሆን የሴማዊ ቋንቋዎች አባል ነው። የቋንቋው መጠሪያ ስልጢኛ በመባል ሲጠራ ስያሜውን ያገኘውም ከብሄረሰቡስም “ስልጤ” ከሚለው ነው።”ስልጤ” በዞኑ በሚገኙ በዋነኛነት አምስትማኅበረሰቦች ማለትም ስልጢ:መልጋ:ሁልባረግ:አዘርነት በርበሬና አልቾውሪሮየጋራ መጠሪያ ነው። በማኅበረሰቦቹ በታሪክ: በማኅበራዊ ኑሮ :በባህል: በቋንቋናበሀይማኖት እንዲሁ ተመሳሳይ ናቸው የስያሜውን መነሻ በተመለከተ የተለያዩመረጃዎች ያሉ ሲሆን ስያሜውን ያገኘው ከሀጂ አሊዬ 5ተኛ ልጅ ከሆኑት ገን-ስልጤ አልያም ሱልጣኔት ከሚለው አረብ ኢስላማዊ መንግስት ጥንታዊነትእንዲሁም ነባር ኢስላማዊ መንግስታትና ማኅበረሰቦች የታሪክወራሽነትንበማሰብ ነው የሚለው በስፋት ይገለፃል::☞ስልጢኛ ቋንቋከሴማዊያን ቤተሰቦች ይመደባል .. ቋንቋው በስፋት ከሀረሪኛና የዛይ ቋንቋ ጋርበጣም ሲመሳሰል በበርካታ የቃላት ትርጉዋሜ ደረጃ ከአረብኛ: አማርኛ ትግርኛአርጎቢኛና ኦሮምኛ ጋርም ይገናኛል:: ሌላው ስልጤ የምትጠራባቸው ተጨማሪስም “እስላም“ ተብሎሲጠራ ፡ ቋንቋውም”እስላምኛ” በመባል በደቡብ ክፍልእስከ ዛሬ ይታወቃል ።በሰሜኑ የሀገራችን ህብረተሰብ ዘንድ ስልጤ ‘ ጉራጌ`ተብሎ የሚታወቅ ቢሆንም ስልጤ የራሱን ዞን ከመሰረተ ጀምሮ ይህ መጠሪያስሙ ላይመለስ ቀርቶዎል።ስልጢኛ ከ6ዐ ዓመት በፊት የአረብኛ ፊደልንበመጠቀም ለጽሑፍ የዋለ ቋንቋ ቢሆንም ከ1967 ዓ/ም ጀምሮ ልዩ ልዩአዋጆች እና የመሰረተ ትምህርት ማስተማሪያ መጽሐፍት የሳባ ፊደልንበመጠቀም በቋንቋው ተተርጉመዋል፡፡ ከ1987 ዓ/ም ጀምሮ የ1ኛ ደረጃየመጀመሪያ ሣይክል የመማሪያ መጽሐፍት በቋንቋው ተዘጋጅተዋል፡፡ በአሁኑሰዓት የትምህርት ቋንቋ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ እንደዚሁም የሣባ ፊደልንበመጠቀም የመማሪያ መጽሐፍት፣ የስልጢኛ መዝገበ ቃላት፣ የስልጤ ሕዝብታሪክ እና ሌሎች መጽሀፍቶች በቋንቋው ተጽፈው አገልግሎት እየሠጡመሆናቸው ቋንቋው በማደግ ላይ ያለ ስለመሆኑ የሚገልፁ እውነታዎች ናቸው፡፡