ማባዛት ማለት ከመደመርመቀነስማካፈል ጋር እንደ አራቱ መሰረታዊ የቁጥር ሂሳብ ስሌቶች የሚታይ ነው። ስራውም አንድን ቁጥር በሌላ ቁጥር ማብዛት ነው።

የማባዛት ምልክት.

የጥንቱ የኢትዮጵያውያን ዘዴ ለማስተካከል

በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲሰራበት የነበረው የማባዛት ዘዴ በምሳሌ እንሆ።

12ን በ13 ለማባዛተ ከፈለግን እንዲህ እናረጋለን፡-

12*13አንደኛውን ቁጥር በ2 ካበዙ በኋላ ሌላኛውን ደግሞ በ2 ያካፍላሉ፣ ተካፍሎ የቀረውን ይተውታል

በሁለት ማብዛት..... በሁለት ማካፈል
12  ................1324  .................648  .................396  .................1

ከዚያ በቀኝ በኩል በሚገኙት የማይካፈሉ (odd) ቁጥሮች ትይዩ ያሉትን የግራ ቁጥሮች ይደምራሉ። በምሳሌያችን ላይ እንደሚታየው 13፣ 3 እና 1 በቀኝ የማይካፈሉ ቁጥሮች ሲሆኑ፣ በነሱ ትይዩ ያሉትን ስንደምር12+48+96= 156

ይህ ዘዴ ለኮምፒውተር ስራ አገልግሎት በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይቻላል ምክንያቱም ከባይናሪ የቁጥር ስርዓት ጋር ተዛማጅነት ስላለው።