ጥሩነሽ ዲዲባባመስከረም 21 ቀን 1978 ዓ.ም. በኢትዮጵያአርሲ ክፍለ ሀገር በቼፋ ወረዳ ከኦሮሞ ብሄረሰብ ነው። ጥሩነሽ ለቤተሰብዋ ከአምስት 3 ናት። የጥሩነሽ አስተዳደግ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነው። ነገር ግን የጥሩነሽ ቤተሰቦች የረጅም ርቀት አትሌቶች ናቸው። አክስቷ ደራርቱ ቱሉ ሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ እና አንድ ጊዜ ደግሞ የ 10000 ሜትር አሸናፊ እና የብዙ አገር አቋራጭ ውድድር አሸናፊ ነበረች። ሌላ አክስቷም በቀሉ ዲባባ ጥሩ ሯጭ ነበረች ጥሩነሽ ልጅ እያለች በበቆጂ ስትኖር። ሌላዋ እህትዋ እጅጋየሁ ዲባባ ከጥሩነሽ ቀደም ብላ መሮጥ ጀምራ ነበር። ጥሩነሽ ዲባባ የቤተሰብዋን ፈለግ መከተል የጀመረችው እድሜዋ ከፍ ካለ በኋላ ነው። ጥሩነሽ ዲባባ ከ ሯጭ ቤተሰብ ብትፈጠርም ለመሮጥ ግን ምንም ፍላጎት አልነበራትም። ቱሉ በባርሴሎና ኦሎምፒክ በ 10000 ሜትር ባሸነፈች በሰባት አመቱ ጥሩነሽ ወደ አዲስ አበባ በ 2000 ዓ/ም መንገድ ጀመረች። ነገር ግን በቀሉ ዲባባ አባል ከሆነችበት ከእስረኞች ማረሚያ ፖሊስ ቡድን ስፖርት መስሪያ ክበብ ውስጥ አስመዝግባት ልምምድ ቀጠለች። ጥሩነሽ ዲባባ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጮች አንዷ ለመሆን በቃች። ጥሩነሽ ዲባባ በ 14 አመት እድሜዋ በጣም ወጣት እና ሰውነትዋም ተሰባሪ ይመስል ነበር። ብዙዎችም በሩጫ ምንም ተስፋ እንደሌላት እና ሩጫው የሚጠይቀውን ጠንካራ ሰውነት የላትም ብለው ያምኑ ነበር። ጥሩነሽ ዲባባ የኢትዮጵያ የረጅም ርቀት ተወዳዳሪ አትሌት ናት። በ 5000ሜትር የአለም ክብረ ወስን ባለቤት ስትሆን በ5000 ሜትር እና በ10000 ሜትር የኦሎምፒክ ውድድር አሸናፊ ናት። ጥሩነሽ አራት የአለም አቀፍ ውድድር እና አምስት የአገር አቋራጭ ውድድር አሸነፊ ናት። በቅጽል ስም “የሕጻን ፊት ያላት ደምሳሽ” በማለት ይጠሩዋታል።

የሜዳሊያ መዝገብ

ጥሩነሽ በ2008 እ.ኤ.አ. በተካሔደው ቢስሌት ጨዋታዎች.
Women's Athletics
 ኢትዮጵያ ተወዳዳሪ
Olympic Games
ወርቅ2012 London10000 m
ወርቅ2008 Beijing10000 m
ወርቅ2008 Beijing5000 m
ነሐስ2004 Athens5000 m
World Championships
ወርቅ2003 Paris5000 m
ወርቅ2005 Helsinki5000 m
ወርቅ2005 Helsinki10000 m
ወርቅ2007 Osaka10000 m
ወርቅ2013 Moscow10000 m
World Cross Country Championships
ወርቅ2003 LausanneJunior race
ወርቅ2005 Saint-GalmierShort race
ወርቅ2005 Saint-GalmierLong race
ወርቅ2006 FukuokaLong race
ወርቅ2008 EdinburghSenior race
ብር2002 DublinJunior race
ብር2004 BruxellesShort race
ብር2007 MombasaSenior race
African Championships
ወርቅ2008 Addis Ababa10000 m
ወርቅ2010 Nairobi10000 m
ብር2006 Bambous5000 m
World Junior Championships
ብር2002 Kingston5000 m

ውድድር ለማስተካከል

ጥሩነሽ ዲባባ የመጀመሪያ አለም አቀፍ የውጪ ውድድር ያደረገችው በ 2001 በአለም አቀፍ አትሌቶች ውድድር ላይ ነው። ውድድሩን ስታካሂድ የ 15 አመት ልጅ ነበረች በዚህ ውድድር አምስተኛ በመሆን ጨርሳለች። በ 2003 በተደረገው የአፍሮ ኤሽያ ውድድር ላይ በ 5000 ሜትር የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች። የጥሩነሽ ዲባባ አስደናቂ ውጤቶች ማምጣት የጀመረችው በአለም አቀፍ አትሌቶች ውድድር ላይ በ 2003 2005 እና 2007 ላይ ነው። ጥሩነሽ በ 2003 በ 5000 ሜትር ተስፈንጥራ በመውጣት የስፔይኗን ማርታ ዶሚኒጌዝ እና የኬንያዋን ኤዲት ማሳያ ቀድማ በመግባት ነው። በወቅቱ የታወቀች አትሌት ባለመሆኗ ውድድሩን ያስተላልፉ የነበሩት እንግሊዛዊ ስቲቭ ክራም እና ብሬንዳን ፎስተር ውድድሩ 100 ሜትር እስኪቀረው አንድም ጊዜ ስሟን ሳይጠሩ ቀርተዋል። በ 2005 ውድድር ላይ ተስፈንጥራ በመውጣት ብርሀኔ አደሬን እና እህታዋን እጅጋየሁን ቀድማ በመግባት የመጀመሪያዋ 5000 / 10000 ሜትር የወርቅ ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች። በ2007 ኦሳካ ላይ በተካሄደው የ 10000 ሜትር ውድድር የቱርክዋን ኤልቫን አቢይ ለገስን ተስፈንጥራ በመቅደም በ 31:55.41 አሽናፊ ሆናለች።በ 2004አቴንስ ኦሎምፒክ5000ሜትር ጥሩነሽ ሶስተኛ ወጥታለች በመሰረት ደፋር እና በ ኢሳቤላ ኦቺቺ በመሸነፍ። በሁኔታው ብዙ ሰዎች ቢበሳጩም የ 19 አመትዋ ጥሩነሽ የመጀመሪያዋ ወጣት ባለ ኦሎምፒክ ሜዳል ኢትዮጵያዊ አትሌት አሸናፊ አድርጓታል። በ2006ወርቃማው ማህበር ውድድር ከስድስት የወርቅ ሜዳሊያ አምስቱን አሸናፊ ሆናለች ። (5,000 ሜ) በዚህም $83,333 ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች።

የጥሩነሽ ዲባባ ሀይለኛ ተፎካካሪ መሰረት ደፋር ናት። ሁለቱንም በአንድ ውድድር ላይ ለማሳተፍ ታስቧል ነገር ግን ብዙ ጊዜ የሚሳካው በውድድር ላይ ብቻ ነው።

የጥሩነሽ ዲባባ የአሯሯጥ ዘዴ በመጨረሻው ዙር ላይ ተስፈንጥሮ በመውጣት ማሸነፍ ነው። በመጨረሻው የ 10000 ሜትር ውድድር ላይ በ 2005 ዓ/ም የመጨረሻውን 400 ሜትር በ 58.33 ሴኮንድስ ነው የጨረሰችው። ጥሩነሽ ዲባባ በአገር አቋራጭ ሩጫም የተሳካ ውጤት አምጥታለች። ጥሩነሽ ዲባባ አለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድር ባሰናዳው አለም አቀፍ የአገር አቋራጭ ውድድር አምስት የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ነች። ውድድሩም የወጣቶች (በላውሳኔ 2003) አንድ አጭር ርቀት (በ ሴይንት ጋልሚየር 2005) እና ሌሎች ሁለት ረጅም ርቀት (በ ሴይንት ጋልሚየር 2005 እና በፉኩኦካ 2006 ) ከ2007 ጀምሮ በየምድቡ አንድ ውድድር ብቻ ይካሄዳል። ጥሩነሽ ዲባባ ሞምባሳ በተካሄደው ውድድር የብር ሜዳሊያ ተሸልማለች። በ ኤዲንበርግ ላይ በተካሄደው የወርቅ ሜዳሊያ በ 2008 ተሸላሚ ናት።

የወርቅ ሜዳሊያ በኦሎምፒክ ለማስተካከል

ጥሩነሽ ዲባባ በ 2008 ኦስሎ በተካሄደው የ 5000 ሜትር በ14 ደቂቃ 11.15ሴኮንድስ በመግባት በውድድሩ አንደኛ በመውጣት የአዲስ ክብረ ወሰን ባለቤት ለመሆን በቅታለች።

ጥሩነሽ ዲባባ በ ነሐሴ 15 2008 በቤጂንግ ኦሎምፒክ በተደረገው የ 10 000 ሜትር ውድድር በ 29:54.66 በመግባት በውድድሩ አንደኛ በመውጣት የአዲስ ክብረ ወሰን ባለቤት ለመሆን በቅታለች። አሮጌው ሰአት 30:17.49 ነበር። የክብረ ወሰኑም ባለቤት የነበረችው የጥሩነሽ ዲባብ አክስት ደራርቱ ቱሉ ነበረች። ይህም ሰአት የተመዘገበው በሲድኔ ኦሎምፒክ2000ዓ/ም ነበር። አዲሱ የጥሩነሽ ዲባባ ክብረ ወስን ሁለተኛው ፈጣኑ የ 10000 ሜትር ሰአት ሲሆን ለአፍሪካ ደግሞ ፈጣኑ ክብረ ወሰን ነው። የቀድሞው የአፍሪካ ክብረ ወሰን (30:04.18) ነበር በ 2003 አለም አቀፍ ውድድር ላይ በ ብርሃኔ አደሬ የተመዘገበ።

ከአንድ ሳምንት በኋላ በነሐሴ 22 2008 በ 5000 ሜትር መሰረት ደፋርን ቀድማ በመግባት በ 15:41.40 የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ለመሆን በቅታለች። በዚህ ኦሎምፒክ በሁለት ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘቷ በአለም የመጀመሪያዋ የሴት አትሌት ሆናለች። በ 5000 እና በ10000 ሜትር በአንድ ኦሎምፒክ አሸናፊ በመሆኗ።

2008 የቤት ውስጥ እና የሜዳ ዜና የአመቱ ታላቅ አትሌት በማለት ሸልሟታል። በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽንም አስደናቂ የሴት አትሌት በማለት ሽልማት አበርክቶላታል። ተመሳሳይ ሽልማት በ 2005 ቀደም ብሎ ተበርክቶላታል።

2009 በጤና ችግር ምክንያት በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ባዘጋጀው አገር አቋራጭ ውድድር በአማን ተሳታፊ ሳትሆን ቀርታለች። እንዲሁም በ 2009 በበርሊን በተካሄደው የአለም አቀፍ ውድድርም አልተሳተፈችም።

በህዳር 15 2009 በዜቬኡቬሌንሉፕ(ሰባት ኮረብታ) በተካሄደው የ15 ኪሎ ሜትር ርቀት ውድድር በኔዘርላንድ ኒጄምገን የካዮኮ ፉኩሺን የ15 ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰን በግማሽ ደቂቃ በመስበር በ 46:28 አሸናፊ ለመሆን በቅታለች። ከ 2005 በኋላ ይህ ውድድር የመጀመሪያዋ ነበር። ይህንንም አገር አቋራጭ የውጭ ውድድር እንደወደደችው ተናግራለች። ነገር ግን በቤት ውስጥ ውድድር እንደምትቆይ ተናግራለች።

በሃምሌ 27 2012 እ.ኤ.አ በለንደን በተካሄደው የ10000 ሜትር የኦሎምፒክ ውድድር 30 ደቂቃ ከ20.75 ሰከንድ ገብታ ውድድሩን በማሸነፍ በኦሎምፒክ ያገኘችውን የወርቅ ሜዳሊያ ቁጥር ወደ ሶስት ከፍ አድርጋለች። በመሆኑም በኢትዮጲያ ውስጥ እጅግ ውጤታማ የሆነ አትሌትነትን ቦታ ከቀነኒሳ በቀለ ጋር ተጋርታለች። በጋጠማት ጉዳት ምክንያት ለ16 ወራት ከውድድር ተገልላ ታህሳስ 2012 ወደ ውድድር የተመለሰችው ጥሩነሽ ውድድሩ ሊጠናቀቅ አንድ ዙር ሊቀረው አካባቢ አፈትልካ በማምለጥ በረጅም ርቀት አሸንፋለች። [1]

የግል ሕይወት ለማስተካከል

ጥሩነሽ ዲባባ ስለሺ ስህንን አግብታለች። ስለሺ ስህን በ2004 እና 2008 የ 10000 ሜትር ኦሎምፒክ ውድድር የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ አትሌት ነው።

ጥሩነሽ ዲባባ ከቤጂንግ ኦሎምፒክ በኋላም የእስረኞች ማረሚያ ፖሊስ ለቡድኑ እና ለሀገርዋ ላደረገችው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የ ሌ/ኮለኔልነት ማዕርግ ተሰጥቷታል። በስሟም በአዲስ አበባ ውጭ ሆስፒታል ተሰይሞላታል።

የአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ውድድር ውጤት

የአልማዝ ማህበር ለማስተካከል

አልማዝ ማህበር በየአመቱ የሚካሄድ የቤት ውስጥ እና የሜዳ ውድድር ነው። ውድድሩም የሚዘጋጀው በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ሲሆን የተጀመረውም በ 2010 ነው።

ጥሩነሽ ዲባባ የ 10,000 ሜትር ድልዋን ስታከብር በ 2007 በአለም አቀፍ አትሌቶች ውድድር.
አመትቦታውውድድሩውጤትሰአት
2010Adidas Grand Prix, New York City5000 m1st15:11.34

የአለም አትሌቲክስ መጨረሻ ለማስተካከል

አለም አትሌቲክስ መጨረሻ በየአመቱ የሚካሄድ የቤት ውስጥ እና የሜዳ ውድድር ነው። ውድድሩም የሚዘጋጀው በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ነው የተጀመረውም በ 2003 እስከ 2009.

አመትቦታውውድድርውጤትሰአት
2003Monaco5000 m3rd14:57.87
2005Monaco5000 m2nd14:46.84
2006Stuttgart3000 m2nd8:34.74
5000 m1st16:04.77
2009Thessaloniki5000 m2nd15:25.92

የወርቅ ማህበር ለማስተካከል

ወርቅ ማህበር በየአመቱ የሚካሄድ የቤት ውስጥ እና የሜዳ ውድድር ነው። ውድድሩም የሚዘጋጀው በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ነው የተጀመረውም በ 1998 እስከ 2009.

አመትቦታውውድድርውጤትሰአት
2002Bruxelles3000 m11th8:41.86
Berlin5000 m6th14:49.90
2003Oslo5000 m3rd14:39.94
Roma5000 m4th14:41.97
2004Bergen5000 m2nd14:30.88
Roma5000 m4th14:47.43
2005Roma5000 m1st14:32.57
2006Oslo5000 m1st14:30.40
Paris Saint-Denis5000 m1st14:54.24
Roma5000 m1st14:52.37
Zürich5000 m1st14:45.73
Bruxelles5000 m1st14:30.63
Berlin5000 m2nd15:02.87
2007Paris Saint-Denis5000 m1st15:21.84
2008Oslo5000 m1st14:11.15
Roma5000 m1st14:36.58

የውጭ ውድድር ለማስተካከል

ውድድርሰአትቀኑቦታው
3,000 m8:29.55July 28, 2006London
5,000 m14:11.15 (WR)June 6, 2008Oslo
10,000 m29:54.66August 15, 2008Beijing
15 km (road)46:28 (WR)November 15, 2009Nijmegen

በቤት ውስጥ ውድድር ለማስተካከል

ውድድርሰአትቀኑቦታው
3,000 m8:33.37January 26, 2008Boston
5,000 m14:27.42January 27, 2007Boston

የቪዲዮ ቃለ መጠይቅ ለማስተካከል

ማጣቀሻዎች ለማስተካከል

  1. ^ "Tirunesh bagged the first Gold Medal at London 2012 for Ethiopia". thearadaonline.com (28 ሃምሌ 2012). Archived from the original on 2016-03-11. በ28 ሃምሌ 2012 የተወሰደ.

ወደ ውጭ የሚያገናኙ ለማስተካከል